Friday, August 1, 2014

የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴግ የደህንነትና የፀጥታ አባላት ከመተማና አብደራፍዕ ሰዎችን እያፈኑ አድራሻው ወደ ማይታወቅ ቦታ እየወሰዷቸው መሆኑ ታወቀ፣፣



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የመከላከያ ሰራዊት ሃላፊዎች ታርጋ ቁጥር 02528 በሆነች ፓትሮል መኪና በመጫን ከትግራይ ምእራባዊ ዞን ጀምረው እስከ ሰሜን ጎንደር ዞን አብደ ራፍዕ እና መተማ እየተዘዋወሩ ሰዎችን እያፈኑ ወደ አልታወቀ ቦታ እየወሰዷቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣፣
  ከዚህ በፊት የአብደራፍዕ’ና የዲማ አካባቢ ነዋሪዎች ከትህዴን ጋር ትገናኛላችሁ ተብለው ታፍነው እንደተወሰዱ’ና ወደ እስር ቤት ተወስደው ከታሰሩም ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር እየተገናኛችሁ ጥይትና መሳሪያ እያቀበላችሁ ነው የሚል ተጨባጭነት የሌለው ውንጀላ እነደቀረበላቸው  የተገኘው መረጃ አስታውቀዋል።
    ታፍነው እየተወሰዱ ያሉ ወገኖች  በየቀኑ እለታዊ ስራቸውን የሚሰሩ የቀን ሰራተኞችና ነጋዴዎች እንደሆኑ መረጃው አክሎ  አስረድቷል፣፣