Wednesday, February 18, 2015

በደሴ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለህወሃት 40ኛ አመት የልደት በዓል የሚሆን ገንዘብ አዋጡ እየተባሉ መሆናቸው ተገለፀ።



እንደምንጮቻችን መረጃ  እኒህ ነዋሪነታቸው  በአማራ ክልል በደሴ ከተማ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ጥር 17/ 2007 ዓ/ም የህወሃትን 40ኛ አመት የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ በድርጅቱ ካድሬዎች በተደረገ ስብሰባ ለበዓሉ ማድመቂያ የሚሆን ገንዘብ አውጡ እንደተባሉ የገለፀው መረጃው ሆኖም ግን ተሰብሳቢዎች የምናዋጣው ገንዘብ የለንም ከአሁን በፊት ምክንያት እየፈጠራችሁ የመዘበራችሁን ይበቃል በማለት እንደተቃወሙት ታውቃል።
በደሴ ከተማ የሚኖሩ ከ30 ሺህ በላይ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ ባለፈው አመት በየካቲት 11 ስም ገንንዘብ አዋጡ ተብለው ከ100 ሺህ ብር በላይ ያወጡት ገንዘብ ለባለስልጣናት የግል ጥቅም መዋሉን ምንጮቻችን ጨምረው አስረድተዋል።