Wednesday, February 18, 2015

በደጉዓ ተምቤን ወረዳ የህወሃት አባልነት ወርሃዊ መዋጮ አልከፍልም ያለውን ወገን የህወሃት ካድሬዎች ጨለማን ተገን በማድረግ ደብድበው በረሃ ላይ መጣላቸውን ተገለፀ።



    የደረሰን መረጃ እንደገለፀው በደቡባዊ ምስራቅ ዞን፤ ደጉዓ ተምቤን ወረዳ ነዋሪ የሆነው መምህር ገብረየሱስ ገብረሂወት የተባለው ወገን ማህበረስላሴ በተባለው ት/ቤት በሚያስተምርበት ሰዓት የህወሃት ወርሃዊ መዋጮ ክፈል ተብሎ አልከፍልም በማለቱ ብቻ አሸባሪ በማለት እንዳስፈራሩትና ጥር 16/2007 ዓ/ም ምሽት ላይ በስርአቱ ተላላኪዎች ጭንቅላቱንና እግሩን በበትር ደብድበው መንገድ ላይ እንደጣሉት ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው በመጨረሻ ይህ በካድሬዎች ተደብድቦ የተጣለውን ንፁህ ዜጋ በነጋታው ቤተክርስቲያን እየሄዱ በነበሩት ነዋሪዎች ወድቆ መገኘቱንና በአሁኑ ሰአትም ሃገረ ሰላም ውስጥ በሚገኘው ሆስፒታል ተኝቶ እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።