Monday, February 16, 2015

የአድዋ ከተማ ነዋሪዎች በከተማው የንግድና ኢድስትሪ ፅህፈት ቤት መጥፎ አሰራር ምክንያት ስራችን ልናሳልጥ አልቻልንም ሲሉ በምሬት ገለፁ።



   ምንጮቻችን እንደገለፁት የአድዋ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑት ወገኖች ንግድ ፍቃድ ለማውጣት ወደ ከተማዋ ንግድና ኢንድስትሪ ፅህፈት ቤት በሄዱበት ጊዜ የፅህፈት ቤቱ ሃላፊዎች በጉቦና በአድልዎ ስለሚፈፅሙት እነዚህ ወገኖች ተቸግረው እንዳሉ ታወቀ።
የአድዋ ከተማ ንግድና ኢድስትሪ ፅህፈት ቤት ሃላፊዎች ጉቦ ለሚሰጧቸውና በዝምድና ለሚቀርባቸው ቀልጣፋ አግልግሎት ሲሰጧቸው ጉቦ ላልከፈሉት ደግሞ እያደናቀፏቸው እንዳሉ የገለፀው መረጃው ለዚህ አግባብነት የሌለው አስራር መፍትሄ እንዲደረግላቸው በማለት ተሰብስበው ወደ ፅህፈት ቤት ሃላፊው አቶ ገብረኪዳን አለምሰገድ በሄዱበት ጊዜ እንደሱ የሚያደርግ ሰራተኛ የለንም ሰማቸውን አታጥፉት በማለት እንደመለሰላቸው ለማወቅ ተችሏል።