በአዲስ አበባ በቲያትር አዳራሽ ጥር 23
/2007 ዓ.ም በፀጋይ በርሀና ኢሳያስ የተካሄደው ስብሰባ በከተማዋና አካባቢዋ ብቻ 10 ሺህ ነባር ታጋይ የትግራይ ተወላጆች ይገኛሉ የሚል ግምት ቢኖራቸውም እንኳን ነገር ግን ከ2000
የማይበልጡ ታጋዮች ብቻ የተሳተፉ ሲሆን የስብሰባው አጀንዳ ደግሞ የየካቲት 11 ታሪክ በእንዴት አይነት አገባብ ይከበር እንዲሁም
መጪው ምርጫ ህብረተሰቡ ለኢህአዴግ እንዲመርጥ የቀድሞ ታጋዮች ህብረተሰቡን እንድትቀሰቅሱ በማለት የስብሰባው አመራሮች በሚገልፁላቸው
ሰዓት በተሰብሳቢዎች ሃይለኛ ተቃውሞ እንዳጋጠማቸው ለማወቅ ተችሏል።
እነዚህ ካድሬዎች መናገር በጀመሩበት ሰዓት-
በስብሰባው ላይ በተገኙ ነባር ታጋይ ወገኖቻችን በበኩላቸው ለምንድን ነው ከዚህ በፊት አይታችሁን የማታውቁት ምርጫ ስለቀረበባችሁ
መነገጃችሁ ልታደርጉን ጥረት እያደረጋችሁ ያላችሁት? ስለየካቲት ታሪክ ደግሞ ለኛ አትንገሩን በትግሉ የነበርን ሰዎች ነን፤ 65
ሽህ የህዝብ ልጆች እንደተሰው እናውቃለን፤ ይህንን የሚያክል መስዋዕት ከፍሎ ህዝባችን ምንም ያገኘው ጥቅም የለም ተከድቶ ነው ያለው
በማለት በጥያቄና በተቃውሞ ለስብሰባው መሪዎች ስላስጨነቋቸው ከስብሰባው እፍረት ተላብሰው ያለምንም ፍሬ እንደወጡ የደረሰን መረጃ
አክሎ አስታውቋል።