Monday, February 16, 2015

የዓረና ትግራይ ኣባል የሆነው አቶ ሕድሮም ሃይለስላሴ አሸባሪ ተብሎ ከሁለት ጣልያናዊያንና አምስት ኢትዮጵያዊያን ጋር እንደታሰረ ታወቀ።



በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ነዋሪ የሆነው የዓረና ትግራይ አባል አቶ ሕድሮም ገብረስላሴ ሁለት ጣልያናዊያንና አምስት ኢትዮጵያዊያን ጥር 15/ 2007 ዓ/ም ከምሽቱ 12፣00 ስአት ወደ ቤቱ ገብተዋል ሰለተባለ ብቻ አሸባሪዎች ናችሁ በማለት እስከ አሁን ድረስ በአፅቢ ወንበርታ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ታስረው እንዳሉ ተገለፀ።
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው አሸባሪዎች የተባሉት የውጭ ዜጎችና ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ አቶ ሙሉጌታ የተባለው የመኪና ሹፌር ይዟቸው የሄዱ ቱርስቶች መሆናቸውን የገለፀው መረጃው የስርዓቱ ካድሬዎች በተደጋጋሚ ለአቶ ህድሮም ገብረስላሴ የሕወሃት-ኢህአደግ አባል እንዲሆን በገንዘብ ሊደልሉት ሞክረው አልሆንም ስላላቸው በአሸባሪ ሊከሱት ፈልገው የፈጠሩት  የከሰረ ዘዴ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።