Monday, February 16, 2015

በሕንጣሎ ወጀራት በማህበር የተደራጁ ሴቶች በአስተዳደሩ ላይ ያላቸውን ቅሬታ እንዳሰሙ ተገለፀ።



እንደምንጮቻችን መረጃ መሰረት በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ሕንጣሎ ወጀራት ወረዳ በዓዲ-ጉዶም ከተማ ነዋሪ የሆኑት በለምለም የባልትና ውጤት ማህበር የሚታወቁ ሴቶች ከአሁን በፊት በማህበር ተደራጅተው መንግስት የገበያ ኔት-ዎርክ እንደሚፈጥርላቸው ቃል እንደገባለቸው ከገለፁ በኋላ አሁን ግን ያመረትነውን ምርታችንን ወደ ገበያ ለማቅረብ አልቻልንም በማለት ጥር 19/ 2007 ዓ/ም ወደ ሚመለከታቸው የአስተዳደሩ አካላት አቤቱታቸውን ባቀረቡበት ጊዜ መንግስት እንድትደራጁ አድርጓል ከዚህ ያለፈ ግን ገበያ የማፈላለግ ስራ የናንተው ፋንታ ነው በማለት የከተማዋ አስተዳዳሪዎች ቃላቸውን እንዳጠፉ ለማወቅ ተችሏል።
እነዚህ ማህበራት በፊናቸው፣ የመንግስት ብድር ስላለን ክፈሉት ካሉንስ ከየት አምጥተን ነው የምንከፍለው እያሉ በከባድ ጭንቀት ላይ ተውጠው እንዳሉ ሊታወቅ ተችሏል።