Monday, February 16, 2015

በመቐለ ከተማ የሚገኙ በጥቃቅንና አነስተኛ ስራ ላይ የተሰማሩ ማህበራት በስርዓቱ ከፋፋይ የአስተዳደር ምክንያት ብሶታቸውን እያሰሙ መሆናቸው ተገለፀ።



ምንጮች ባደረሱን መረጃ መሰረት በመቐለ ከተማ ነዋሪ የሆኑት በአነስተኛና ጥቃቅን ስራ ላይ ተሰማርተው የሚንቀሳቀሱ ማህበራት ቀዳማይ ወያነ ተብሎ በሚጠራው ክፍለ ከተማ ውስጥ እየተሰራ ያለውን የድንጋይ ንጣፍ መንገድ ኮንትራት ስጡን ብለው በጠየቁበት ሰዓት ለናንተ አንሰጥም በክፍለ ከተማው ያሉትን ማህበራት ብቻ ነው የምንሰጠው ስለተባሉ ከሌሎች ክፍለ ከተማ የመጡትን ማህበራት ስለከለከላቸው ምሬታቸውን እያሰሙ እንደሚገኙ   ለማወቅ ተችሏል።
   እነዚህ ማህበራት መፍትሄ እንዲያገኙ በማለት ወደ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ በመሄድ አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም የክፍለ ከተማዋ አስተዳዳሪ የሆነችው ወ/ሮ አስኳል ረዳ ሌላ ቦታ ሄዳችሁ ስሩ እንጂ እዚህ አትሰሩም በማለት እንዲመለሱ ማድረጓንና ማህበራቶችም ከሃገራችን አለፍን የት ሂደን እንሰራለን በማለት ሃሳባቸውን በምሬት እንደገለፁላት መረጃው አክሎ አስርድቷል።