Friday, April 3, 2015

ለ5ኛ ጊዜ በሚካሄደው ምርጫ የመከላከያ ሰራዊት የምርጫ ካርድ እንዲይዝ እየተገደደ መሆኑን ምንጮቻችን ከተለያዩ አካባቢዎች ገለፁ፣

  ለ5ኛ ጊዜ ሊካሄድ ታስቦ ባለው የይስሙላ ምርጫ ላይ  እንዲሳተፉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በስርዓቱ የሰራዊት አዛዦች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ እየተገደዱ መሆኑን የገለፀው መረጃው። ወታደሩ በነፍስ ወከፍ የምርጫ ካርድ እንደያዘና ፎርም እንደሞላ ለማረጋገጥ ፍተሻ እየተደረገ ሲሆን ይህንን ተከትሎ ሰራዊቱ ተግባሩን ስላልተቀበለው ምርጫ መብት እንጂ ግዴታ አይደለም በማለት ውስጥ ለውስጥ ከባድ ጥያቄ እያነሳ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል፣
  እንደዚህ አይነት ጥያቄ እያነሱ ከሚገኙት የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል። አስር አለቃ አስፋው የተባለው “የመከላከያ ሰራዊቱ እንዲመርጥና ድምፁን ለኢ.ህ.አ.ዴግ እንዲሰጥ ለምን በግልፅ አታውጁም” በማለቱ። ከ22ክፍለ ሰራዊት በስውር ከተወሰደ በኋላ እስካሁን የት እንዳለ እንደማይታወቅ ለማወቅ ተችሏል፣