Thursday, April 16, 2015

በኢህአዴግ እርሻ ፖሊሲ የሚረጋገጥ እድገት የለም!!



የአገራችን የእርሻ ሁኔታ ለዓመታት ሲሰራበት ከቆየው ባህላዊ አጠቃቀም መውጣት ባለመቻሉ ምክንያት። ከግዜ ወደ ግዜ እየተበራከተ ያለውን ህዝብ ፍላጎት ሟሟላት አልቻለም፣
    ይህን ኃላ ቀር  የእርሻ አጠቃቀም መቀየር ስላልተቻለም። እዚህ ግባ የሚባል ምርት እንዲገኝና መልካም የአዝመራ ወቅት ነበር በተባለለት ግዜም ቢሆን ለአመት ቀለብ የሚሆንም ሊያገኝ አልቻለም፣ በዚህም ምክንያት ከመጋቢትና ሚያዝያ ወር በኃላ ገና ክረምት እንኳን ሳይገባ ጎተራውን አማጦ ወደ ስደት የሚያመራበት ሁኔታ ነው ያለው፣
    ወደ ሩቅ ሳንሄድ ከሃይለስላሴና ከደርግ ስርዓት ጀምሮ። እስካሁን ያለውን ሁኔታ ስናየው። ህዝቡ የክረምት ዝናብ በመጠበቅ ብቻ እርሻውን ስለሚያከናውንና። የዘመናዊ እርሻ ተጠቃሚ መሆን ስላልቻለ። አገራችን ስልጣን ላይ በወጡ ፀረ ህዝብ አመራሮች ምክንያት። የረሃብና የድርቅ ተምሳሌት ተደርጋ በመዝገበ ቃላት ውስጥ እንድትሰፍርና። ዜጎቻችን በተለያዩ አገሮች ተሰደው እንዲዋረዱና በላያቸው ላይ ከፍተኛ በደል ሊፈጸምባቸው ችሏል፣
   የወያነ ኢህአዴግ ያገዛዝ ስርዓት። ስልጣን ላይ ከወጣ ሩብ ክፍለ- ዘመን ቢያስቆጥርም። በእርሻ በኩል ያለው ተጨባጭ ደረጃ ስናይ ግን። ለፖለቲካ ፍጆታ ተብሎ ከመነገሩ ውጭ። ቀደም ብለው ከነበሩ ስርዓቶች በላይ ለውጥ ተረጋግጧል ተብሎ የሚነገርለት አይደለም፣ በአፄ ሃይለስላሴና በደርግ ስርአት ግዜ እያጋጠመ በነበረው ተከታታይ ድርቅ አያሌ ህዝብ ሂወቱ ያጣና ይሰደድ ነበር፤ አሁን በኢህአዴግ ስርአት ቢሆንም በተመሳሳይ መንገድ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን መንግስት በሚከተለው ኃላ ቀር የእርሻ አጠቃቀምና ጤነኛ ያልሆነ ፖሊሲ። ህዝቡ በረሃብና በበሽታ ምክንያት እየሞተና እየተሰደደ ያለበት ሁኔታ ላይ ይገኛል፣
    እንደ ኢህአዴግ ስርዓት አገላለፅ። እርሻ መር የሆነውን የአገሪቱ  ኢኮኖሚያው እድገት። ይህን ያህል ፐርሰንት እስመዘገበ በሚል የሃሰት ሪፖርት። በአለም ውስጥ ከሚገኙና ቀልጣፋ እድገት ካስመዘገቡ አገሮች ተርታ እንድንቀመጥ ችለናል፤ እርሻችን አጥጋቢ በሆነ መንገድ እየተጓዘ ነው፤ የምግብ ዋስትና አረጋገጥን፤ የመስኖ እርሻ አጠቃቀማችን  ከግዜ ወደ ግዜ እድገት እያሳየ ስለሆነ። አጠቃላይ ለእርሻ ከሚውል መሬት ግማሹን ያህል በመስኖ ስራ ላይ እንዲውል በማድረግ። የአገራችን አርሶ አደር ሚሊዮነር እስከመሆን ደርሰዋል ወ,ዘ,ተ እያሉ። የሃሰት ድርሰቶች ሲያሰሙን እያደመጥናቸው ነው፣
    ነገር ግን። የኢህአዴግ መሬዎች የሚናገሩትና በተጨባጭ መሬት ላይ ያለው ሃቅ የማይገናኙ ሁለት ጫፎች በመሆናቸው። የስርዓቱ ባዶ ተስፋዎች መጨረሻ የላቸውምና። የህብረተሰባችን የድህነት ደረጃ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ በመሄዱ ምክንያት። ህዝቡ በከፋ የንሮ ደረጃ ላይ እንዲኖር የተገደደበት ሁኔታ ላይ ይገኛል፣

ለማጠቃለል።-
-    ያገራችን የእርሻ ፖሊሲ። አጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ ንሮውን ከእጅ ወደ አፍ እንዲሆን ያደረገና። ከኃላ ቀር ባህላዊ የእርሻ አጠቃቀም ማውጣት እንዳልቻለ፤  
-    ባገራችን ውስጥ ያለው የትምህርት ፖሊሲ ብልሹ ከመሆኑ በላይ። ተንግብተዋል የሚባሉት ትምህርት ቤቶችም እኩል በሆነ መንገድ ስላልተገነቡ። በትምህርትና በእውቀት የተደገፈ እርሻ መር ክፍለ ኢኮኖሚ መገንባት እንዳልተቻለ፤
-     አብዛኛው በገጠር የሚኖረው ወጣት። የእርሻ መሬት ስለሌለውና በስራ አጥነት ምክንያት ወደ ከተሞችና ስደት ለምሄድ እየተገደደ መሆኑ፤
-    ባገራችን የሚገኘውን ሰፊና ለም መሬት። በቀዳሚነት ያገር ተወላጆች ለሆኑ ባለሃብቶች ከመስጠት ይልቅ። ለረጅም ዓመታት ሲጠቀሙበት የቆዩትን ድሃ ወገኖቻችን እያፈናቀልክ። ለውጭ ኢንቨስተሮች እንዲሰጥ በመደረጉ ምክንያት። አገራችን ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንዳታገኝ ተደርጓል የሚሉና ሌሎች እየተፈጸሙ ካሉት ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው፣
ስለዚህ ያገራችን አርሶ-አደር። መብቱና ነፃነቱ ተነጥቆ። እንደአማራጭ ሌላውን የተሻለ መንገድ እንዳይጠቀም እድሎቹ የተዘጋ በመሆኑ። ሚሊዮነር መሆን ይቅርና። በህወሃት የተሳሰተ የእርሻ ፖሊሲ ምክንያት በላዩ ላይ አድልዎና የመልካም አስተዳደር እጦት ተጮምሮበት ብሶቱን እያሰማ ባለበት ባሁኑ ግዜ። ፍላጎቱን የረገገጥለታል ብሎ ማሰብ የሚቻል አይደለም፣