ይህ ግንቦት 16/2007 ዓ.ም በሃገር አቀፍ
ደረጃ ሲካሄድ የዋለው የይስሙላ ሃገራዊና ክልላዊ መረጫ በትግራይ ክልልም ሲካሄድ መዋሉን የገለጸው መረጃው ይሁን እንጂ ወደ ምርጫ
ጣቢያው ተመሳስለው የገቡ የገዥው ቡድን የደህንነት አባላት ሊመርጥ የገባውን ህዝብ የምርጫ ካርዳችሁና የመታወቂያ ወረቀታችሁን አሳዩ
በማለትና ከህወሃት ኢ,ህ,አ,ዴ,ግ ውጭ ሌላ ድርጅት እንዳትመርጡ ለቀጣይ ህላዌአችሁን አስቡላት በንብ ላይ ምልክት አድርጉ እያሉ
እያስፈራሩቸው እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል።
መረጃው ጨምሮ እንዳስረዳው ይህ ሊመርጥ የገባ ህዝብ የምርጫ ህግ በሚለው
መሰረት ለምን ዲሞክራሲያዊ መብታችንን ተጠቅመን የመሰለንን እንድንመርጥ እድል አይሰጠንም፤ እስከመቼ ነው በታጣቂዎች እየተጠበቅን
ህወሃት ኢ,ህ,አ,ዴ,ግ,ን እየመረጥን የምንኖረው በማለት በምሬት እየገለጸ መዋሉና በተለይ የዜጎችን ነጻነት የሚጥስ ፍትሃዊነት
የጎደለውን ተግባር የታዘቡ ዜጎቻችን ለሆዳቸው ባደሩ የስርዓቱ ተላላኪዎች ተግባር ተቆጥቶው እንዲህ በማድረግ ታማኝና ሰላማዊ ምርጫ
ሊካሄድ አይችልም በማለት ሳይመርጡ ተመልሰው እንደሄዱ መረጃው አክሎ አስረድቷል።