በኦሮሚያ ክልል ደንቢደሎ ከተማ የሚገኙ የተቃዋሚ
ድርጅት አባላትና የምርጫ ታዛቢ ዜጎች ግንቦት 16/ 2007 ዓ/ም ሲካሄድ በዋለው የይስሙላ ምርጫ ላይ በስርአቱ ታጣቂ ሃይሎች
በዱላ እየተቀጠቀጡ ከምርጫ ጣቢያው እንደተባረሩ ከአካባቢው የተገኘው መረጃ አመለከተ።
ከዚህ በመነሳትም የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ ይህንን አስነዋሪ ተግባር በመቃወም
ምርጫውን ትቶ ተቃውሞ እንዳስነሳ የገለፀው መረጃው ይሁን እንጂ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በፖሊስ አባላትና በወታደሮች ህዝቡን እየቀጠቀጡና
ሲያስፈራሩት እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል።
በተመሳሳይም-ሃገራዊና ክልላዊ ተብሎ በሚጠራውና ለአምስተኛ ጊዜ ግንቦት
16 2007ዓ/ም በተካሄደው አስመሳይ ምርጫ ላይ በኦሮሚያ ክልል አርጆ ከተማ መድረክን ወክለው በከተማዋ ለሚካሄደው ምርጫ እንዲታዘቡ
ተሰማርተው የነበሩ ገረመው እጀታና ተሾመ ጉለማ የተባሉ ወገኖች በስርዓቱ የፖሊስ ታጣቂ ሃይሎች ተደብድበው ከባድ ጉዳት ድርሶባቸው
ከታዛቢነት ውጭ እንደሆኑ ተደርገዋል።
እነዚህ የመድረክ ፓርቲ ተቋዋሚ አባላት የሆኑት ዜጎች ከመርጫ ታዛቢነት
በታጣቂ አባላት መባረራቸው ሳይበቃ ገመቹ እጀታ የተባለው ወገን በዚህ ሃላፊነት የጎደለው ተግባር አይኑ የጠፋ ሲሆን ተሸመ ጉለማ
የተባለ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶበት እያለ ወደ እስርቤት አስገብተው እያሰቃዩት እንዳሉ መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።