Sunday, May 31, 2015

የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ቦንጋ አካባቢ የነበረ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት እንዲቃጠል ማድረጋቸው ተገለጸ።



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት በደቡብ ክልል ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ ሰፊ የተፈጥሮ ጫካ በአካባቢው ህዝብ ለዘመናት ጠብቆት የኖረ ሃብት ሲሆን የገዢውን ስርአት በመቃወም እየታገሉ ያሉት ተቃዋሚዎች የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ነው ብለው ስጋት ላይ የወደቁት የስርአቱ ካድሬዎች እሳት ለኩሰው እንዲቃጠል ማድረጋቸውና ይህን እኩይ ተግባር የታዘበው የአካካባቢው ህዝብም በስርአቱ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳስነሳ ለማወቅ ተችሏል።
   የአካባቢው ህዝብ እየተቃዎመ በነበረበት ሰዓት እንደገለፀው በአፋችሁ ልማት አልሙ፤ ድህነት አጥፉ እያላችሁ በተግባር ግን መተኪያ የሌላቸውን የተፈጥሮ ሃብቶችን እያቃጠላችሁ ነው በማለት ሃይለኛ ተቃውሞ ማንሳታቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።