Thursday, May 14, 2015

በደቡብ ወሎ ዞን ወረ-ኢሉ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ ወገኖቻችን መሬታቸውን ያለአግባብ በመነጠቃቸው ምክንያት የአካባቢውን አስተዳዳሪ መኖሪያ ቤት አቃጥለውት እንደተሰወሩ ተገለፀ።



    በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ወረ-ኢሉ ወረዳ ቱሉ በተባለ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ አንተነህና ሰኢድ ከተማ የተባሉ ወንድማማቾች በህጋዊ መንገድ ተሰጥቷቸው ግብር ሲከፍሉበት የነበረ መሬታቸውን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በአካባቢው አስተዳዳሪ ስለተቀሙ የአስተዳዳሪውን መኖሪያ ቤት ከነሙሉ ንብረቱ በማቃጠል ከአካባቢው እንደተሰወሩ ምንጮቻችን ገልፀዋል።
    የቱሉ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ዜጎቻችን መሬታችን ይመለስልን ብለው ስለጠየቁ ብቻ ለ15 ቀናት መታሰራቸውን የገለጸው መረጃው ለጥያቄዎቻቸው ተገቢውን መልስ የሚሰጥ አካል ባለማግኘታቸው ምክንያትም ጠቅላላ ንብረታቸውን በመሸጥና የአስተዳዳሪውን ንብረት በማቃጠል ከአካባቢው እንደተሰወሩ የደረሰን መረጃ አስታወቀ።