የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ግንቦት 16 ለአምስተኛ ጊዜ የሚካሄደውን
ክልላዊና ሃገራዊ አስመሳይ የኢህአዴግ ምርጫ ለመወዳደር በእንቅስቃሴ ላይ ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲዎች ከህዝብ ጋር ተገናኝተው ቅስቀሳ
በማካሄድ ደጋፊዎችን እንዳያገኙ ስርዓቱ የተለያዩ ሴራዎችን እየፈጠረ እያሰናከላቸው ሲሆን በተለይ ደግሞ በመቀሌ ከተማ ለመወዳደር
በእንቅስቃሴ ላይ ያሉት ድርጅቶች ቅንጅትና ኢዴፓ በዚህ ሳምንት ውስጥ ህዝብ ለመቀስቀስ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚጠይቁበት ሰዓት በህወሃት
ኢህአዴግ ካድሬዎች እንደተከለከሉ ምንጮቻችን ገለፁ።
መረጃው ጨምሮ
እንደገለፀው በከተሞች ላይ ተከስቶ ባለው የመብራት መቆራረጥ ምክንያት በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ ፋብሪካዎችና የንግድ ተቋማት ለከባድ
ኪሳራ እየተጋለጡ መሆናቸውን የገለፀው ይህ መረጃ። በዚህም የተነሳም የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ ዕለታዊ የምግብ ማብሰያ አጥቶ እየተቸገረ
እንደሚገኝና የተለያዩ ንብረቶችም በድንገታዊ የመብራት መቆራረጥ ምክንያት እየተቃጠሉ ባሉበት ሰዓት ሃላፊነት ወስዶ ካሳ የሚሰጥ
አካል ባለመኖሩ ነዋሪው ህብረተሰብ ምሬቱን እያሰማ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል።