የህወሃት ኢህአዴግ ካድሬዎች ለመቀሌ ከተማና
ለአካባቢው ህዝብ በተደጋጋሚ ከዕለታዊ ስራዎቻቸው እያሰናከሉ በምርጫ ቅስቀሳ ስራ ላይ እያዋሏቸው እንደሚገኙ የገለፀው መረጃው ለሰማያዊ
ፓርቲ እንዳትመርጡ ሰማያዊ ፓርቲ አይ ኤስ ከተባለው አሸባሪ ቡድን ጋር ግንኙነት ያለው ስለሆነ ለኢህአዴግ ምረጡ እያሉ ለህብረተሰቡ
ከእውነት የራቀ መረጃ እየሰጡት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ህብረተሰቡ ግን በስራችን ላይ ትኩረት እንዳናደርግ ለኢህአዴግ ምረጡ እያሉ
በተደጋጋሚ ስብሰባ ላይ ተጠምደን እንድንውል ያደርጉናል እያለ በማማረር ላይ እንደሚገኝና ከኢህአዴግ በላይ ለኢትይጵያ ህዝብ ያሸበረ
ቡድን የለም በማለትም በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በግልፅ እያስቀመጡ መሆናቸውንም ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል።