በያዝነው 2007 ዓ.ም ግንቦት ወር ላይ
የተካሄደው
አገራዊ
ምርጫ
በገዢው
ፓርቲ
እንዲሁም
በተቃዋሚ
ፓርቲዎች
ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውና ምርጫ
ቦርድም
ምርጫውን
በበላይነት
ለመምራት
ቁሳዊና
ቴክኒካዊ
ዝግጅቶችን
እንዳደረገ
የገዢው
ፓርቲ
ልሳን
በሆነው
በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሮሽን /EBC/ በተደጋጋሚ
ተሰምቷል።
ይህን ተከትሎ
እንደ
ከዚህ
ቀደሙ
ሁሉ
በተቃዋሚ
ፓርቲዎች መካከል ውስጣዊ
መከፋፈል፤ አለመረጋጋቶችና ምርጫው አሁንም ካለፉት
የምርጫ
ተሞክሮዎች
በመነሳት
የገዢው
ፓርቲ
ረጃጅም
እጆች
እንደነበሩበት መተንበይ
አዳጋች
አልነበረም።
ባገራችን ውስጥ ያሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች ለምርጫው ያደረጉት ቅድመ ዝግጅት
በገዢው
ፓርቲ
ጥብቅ
ክትትል
ስር
ሲሆን
ፓርቲዎቹ
የሚደርስባቸውን ጫና
ለመቋቋም
እንዲሁም
ጠንካራ
ተፎካካሪ
ለመሆን እንዲያስችላቸው ውህደት በመፈጸሙ ላይ በሚፈለገው ፍጥነት እየተጓዙ እንዳልነበሩና በተካሄደው ምርጫም በሃገር ውስጥ ትልቅ ግምት ከሚሰጣቸው እንደ አንድነት፤ መድረክ፤ ሰማያዊ ፓርቲና የመሳሰሉት በገዢው ፓርቲ ተደጋጋሚ ትንኮሳ እንደደረሰባቸውና ይህ ድርጊትም በምርጫው ዋዜማ ላይ አይሎ መታየቱ ይታወቃል።
ለመሆን እንዲያስችላቸው ውህደት በመፈጸሙ ላይ በሚፈለገው ፍጥነት እየተጓዙ እንዳልነበሩና በተካሄደው ምርጫም በሃገር ውስጥ ትልቅ ግምት ከሚሰጣቸው እንደ አንድነት፤ መድረክ፤ ሰማያዊ ፓርቲና የመሳሰሉት በገዢው ፓርቲ ተደጋጋሚ ትንኮሳ እንደደረሰባቸውና ይህ ድርጊትም በምርጫው ዋዜማ ላይ አይሎ መታየቱ ይታወቃል።
ያገራችን ህዝብ
ካለፉት
የምርጫ
ጊዜያቶች
በተለየ
ሁኔታ
የፓለቲካ
አድማሱ
የሰፋበትና
በማሕበራዊ
ድህረ
ገፆች
የሚለቀቁ
የተለያዩ
ክርክሮች፤
በግል
ፕሬሱ
ይታተሙ የነበሩ
የፖለቲካ ትንታኔዎች፤ ከገዢው ፓርቲ እየሾለኩ
የሚወጡ
የተለያዩ
መረጃዎች
እንዲሁም
ህብረተሰቡ
አማራጭ
ምንጭ አግኝቶ በተሻለ መንገድ ሁኔታውን እየገምመገመ
ያለበት ሁኔታ ላይ ቢገኝም። ስርዓቱ በዘረጋው የአፈና መረብ ምክንያት ምርጫው ነፃ፤ ገለልተኛ፤ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ
መንገድ ሊከናወን አልቻለም።
በመሆኑም
ማሕበረሰቡ
ምርጫው
በገዢው
ፓርቲ
በተለመዱ
ማጨበርበሮች እንደተጠናቀቀ አውቆ እንደ ባለፉት
የምርጫ
ጊዜያቶች
በቸልታ ማየትና በላዩ ላይ በሚፈፀሙ የማስፈራራት ዛቻ
ሳይንበረከክ እስከ መጨረሻው የለውጥ ሃዋርያነቱን በተጠናከረ ሁኔታ ወደ ፊት ማስቀጠል ይኖርበታል፣ ህዝቡ መንግስት
የሚያካሂደውን
የመብት
ረገጣ፤ አድሎአዊ አገዛዝ፤ ሙስና፤
እንዲሁም
በእስልምና
ሀይማኖት
እና በኦርቶዶክስ የዕምነት ተከታዮች ላይ እጁን በማስገባት እየፈፀመ ያለውን
በደል
በሚገባ
ስለሚያውቅ
ስርዓቱ ጉልበት ያለው
ቢመስልም
ውስጡ
ግን
ባዶ
አባላቱ
በጥቅም፤ እንዲሁም በመልካም አስተዳደር
እጦት
ያኮረፉ
የሚበዙበትና ገዢው
ፓርቲ
ከህወሓት ውጭ ያሉ
ፓርቲዎችን
በአይነ
ቁራኛ
መመልከቱና
አብዛኛውን
ስልጣን
ጠቅልሎ
መያዙ
በአጋር
ድርጅቶች
ጥርስ
ውስጥ
እንዲገባ ምክንያት ሆኗል።
ለማጠቃለል-
የማሕበረሰቡ
ንቃተ
ህሊና
በጨመረበት፤ ገዢውን
ፓርቲ
ተጨባጭ
ባልሆኑ መረጃዎች ህዝቡን እየወነጀለ ባለበትና መንግስት በተደጋጋሚ የሚፈፅማቸው የሰብዓዊ
መብት
ረገጣዎች በባሰ መልኩ እየቀጠለ ባለበት ሁኔታ ምርጫው
በኢህአዴግ አሸናፊነት ይጠናቀቃል ብሎ ማሰብ አይቻልም፣ ነገር ግን
ገዢው
ፓርቲ
በምርጫ
ቢሸነፍም ስልጣኑን ለመልቀቅ ፍቃደኛ
ባለመሆኑ
ድምፁ
የተሰረቀበት ማሕበረሰብ
አልመረጥኩም ብሎ
መቃወምና በከፍተኛ ሁኔታ ድምፁ ማሰማት ይጠበቅበታል።
ምክንያቱም ገዢው
የኢህአዴግ ስርዓት የምርጫውን
ውጤት
በጸጋ
ተቀብሎ
ለመጪዋ
ኢትዮጵያ
ዘላለማዊነት በቅን
ልቦና
ምርጫውን
ለግል ጥቅም ሳይሆን የህዝቡን
ድምፅ
እንዲከበር
ልባዊ
ምኞትና ፍላጎት ስለሌለው የግድ ድምፁን ማሰማት
ይኖርበታል።