Wednesday, December 16, 2015

በጎንደር ከተማ የሚገኝ እስር ቤት በህዳር 21/ 2008 ዓ/ም በእሳት ቃጠሎ ስለጋዬ በውስጡ የነበሩ እሱረኞች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸዉን ምንጮቻችን ከከተማው ገለፁ።



  በምንጮቻችን ገለፃ መሰረት በጎንደር ከተማ ውስጥ የሚገኝ  እሱር ቤት ምክንያቱ ባልታወቀ  በእሳት  ስለጋዬ በውስጡ የነበሩ እስሮኞች ከአደጋዉ ለማምለጥ በመኮሩበት  ግዜ በጥበቃ ዙርያ ተሰማርተው የነበሩ ፖሊሶች ሰለ ከለከልዋቸው  ከባድ ጉዳት  መድረሱን ጠቅሰው በቃጠለው ከ17 በላይ እሱረኞች  ወድያውኑ ህይወታቸውን ሲያልፍ በ700 የሚሆኑ እሱረኞች ላይም ከባድና ቀላል ጉዳት  መድረሱና በዚህ ቃጠሎ የደነገጠው የከተማው ነዋሪውም ቃጠሎውን  ለማጥፋት በመኮረበት ግዜ ፖሊሶቹ የሩምታ ተኩስ በመክፈት  ለህዝቡ  በማባረራቸው በአደጋው የተጠቁ  የእሱረኞች  ቁጥር ሊጨምር መቻሉ ታወቀ።
    መረጃው ጨምሮ  እንዳስረዳው በቃጠለው ከሞቱት  እሱረኞች መካከል ኣዲሱ  የተባለ የማይ ፀብሪ ተወላጅ  የሚገኝባቸው ሲሆን እሱም ዕድሜ ይፍታህ ተፈርዶበት እንደነበረና  ሌሎች  እሱረኞችም ከአደጋው ለማምለጥ በመኮሩበት ግዜ በፖሊሶቹ በተተኮሰው ጥይት የሞቱ እንዳሉ ጠቕሶ እንዳይረዳ የተከለከው ህዝብም በእስሮኞቹ  ላይ የደርሰው ጉዳት  በጣም እንዳስቆጣውና ይህ የተነሳው የእሳት ቃጠሎም ፖሊሶቹ ሆን ብለው የፈፀሙት ነው ሲል ምሬቱን ብመግለፅ ይገኛል።