ገዢው የኢህአዴግ ስርአት የኢትዮጵያ ህዝቦች ለመከፋፈል የቅማንት ብሄረሰብ
ልዩ ዞን ኣድርጎ እንዲያሰፍራቸው እየሰራለት እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው። ስርኣቱ የአማራ ህዝብ ከቅማንት ብሄረሰብ እንዲጣላና
እንዲከፋፈል በመስራት ላይ የቆየ ሲሆን። በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ስርአቱ በሚጠቀምበት ተንኮል የሁለቱን ብሄረሰቦች ተወላጆች መካከል
በከባድ ግጭት ተጠምደው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ስርአቱ ራሱን እየገደላቸው የቅማንት ብሄረሰብ ተወላጆች የአማራ ብሄረሰብ
ናቸው የገደሏቸው በማለት ወገኖች እርስ በራሳቸው እንዲገዳደሉ በማድረግ ላይ ባለበት ጊዜ። አጋጣሚውን በመጠቀም ተላላኪዎቹን በማሰማራት
በድብቅ የገደላቸው የቅማንት ብሄረሰብ ተወላጆች ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ለማጣላትና ለፕሮፖጋንዳ ስራ አስከሬኑን እየተጠቀመለት እንዳለ
ታወቀ።
በዚህ ሳምንት የአማራ ህዝብ ለመከፋፈል እያደረገው ያለ እንቅስቃሴ
አካባቢውን የጦርነት አውድማ አርጎት እንደሚገኝና በዚህ ሳቢያም እየተካሄደ ባለው ግጭት ዋስትና ያጡት ሴት እህቶቻችንና ህፃናት ቄያቸውን ትተው ወደ ጎንደር ከተማ
ሲጓዙ በመንገድ ላይ እየንተጠባጠቡ እንደሚገኙ መረጃው አክሎ አስረድቷል።