የኢህአዴግ መሪዎች መስረተ ልማት በሚል ሽፋን ተጠቅመው የህዝብን ጥቅም መሰረት ያላደረገና የዜጎችን ጥቅም
የሚጋፋ፣ የስልጣን ዕድሜያቸውን ለማራዘም በየጊዜው የሚያወጡትን
ለህዝብ የማወክል አዋጅ ተከትሎ፣ ዜጎች የመብት ጥያቄ ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ የኢህአዴግ መሪዎች ደግሞ ካለፉት ስርአቶች
በከፋ መልኩ በጥይት እሩምታ ከጨፈጨፉት ሩብ ዘመን አስቆጥረዋል።
በዚህ ሳብያም ይህ እኩይ ተግባር በሃገርና በህዝብ ላይ ከባድ የሚባል
የገንዘብና የንብረት ኪሳራዎችን በማውረድና ለበርካታ ንፁኃን ወገኖቻችን ህይወት በየጎደናው ተቀዝፈዋል።
በዚህ ሳምንት ደግሞ ገዢው ስርአት ቀደም ብሎ አውጥቶት የነበረውን የከተሞችን
ማስተር ፕላን አዋጅ፤ አስቀድሞ ከህዝብ ጋር ሳያወያዩ በድንገት በአዲስ አበባ ፊንፊኔና በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ያለ ምንም
ማስረጃና ግንዛቤ ለመተግበር መነሳቱ ተከትሎ የሃርሚያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፤ የነቀምት ከተማ ህዝብ፤ የአዳማ፤ የአስላ፤ የአምቦ
ከተማ፤ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፤ የግንቢና በሌሎች ከተሞች ህጋዊነትና የህዝብ ድጋፍ የሌለው የህዝብን ጥቅም በማያረጋግጥ ማስተር
ፕላን ላይ በመቃወም ሰላምዊ ሰልፍ ወጥተዋል።
ይህ የህዝቦችን ጥቅም የማያስቀድም እንቅስቃሴ ለማገት የተነሳው የህዝብ
ተቃውሞ ለማደናቀፍ የስርአቱ የፀጥታ ሃይሎች በወሰዱት የሃይል እርምጃና
በተኮሱት ጥይት ንፁሃን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ሰላምዊ ህዝብ ገድለው። በሌሎችም ተማሪዎች ላይም ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ሲደርስባቸው የተቀሩትም ደግሞ በእስር ቤት ታጉረው በስቃይ ላይ ይገኛሉ። ይህንን ተግባር ደግሞ የትግራይ
ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ በጥብቅ ይኮንነዋል።
የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፣ ይህ ሁኔታ መቋጫ ስላልተበጀለት በኢህአዴግ ገዢዉ ቡዱን ላይ የተነሳው መጠነ ሰፊ ተቃውሞ ከኦሮሚያ ክልል
ተወላጆች አልፎና ከስርአቱ ቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ወደ ሌሎች የአገራችን ከተሞች ሊስፋፋ ችሏዋል።
የዚህ አይነት አስተያዬትና የህዝብን ስሜት ማእከል ያላደረገ አካሄድ ገዢው
ስርአት በትግራይ ህዝብ ላይ በሰፊው እየሰራለት እንኳ ቢሆንም፣ የትግራይ ህዝብ ግን አፍ አውጥቶ በአንድነት በመቆም ችግሩን አንስቶ
እንዳይናገር፤ እንዳይቃወምና እንዳይደራጅ የተለየ ልጓም ተበጅቶለትና
ተጨቁኖ እየኖረ ያለ በመሆኑ እንጂ፣ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች
ወድሞቹ የኢትዮጵያ ህዝብ የተለየ ሱጦታና ጥቅማ ጥቅም እንደማያገኝ የሚታወቅ ሆኖ፣ በዚህ መልክ ደግሞ የኢህኣዴግ ስርአት ለትግራይ
ህዝብ የሚወክል እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል።
ይህ ሊታፈን የማይችል የህዝብ ስሜት በአጭር ግዜ ውስጥ ፈንድቶ ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያመጣ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል፣ ይህ በህዝብና
በሃገር ላይ የተጣለው አፈናና የሚፈጠሩትን አደጋዎችና ውድቀት ሊቆም ከሆነ ለዚህ ችግር ጠንቅና የህዝብ ሃላፊነት የሌለው ገዥው
የኢህአዴግ ስርአት ከስልጣን ሲወገድ ብቻ ነው፣
የተከበርክ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፣ ይህንን ሃቅ በማመንና ለውጥ ፈልገህ የምታካሄደው
ፀረ ገዢው የኢህአዴግ ስርአት የተቃውሞ ሰልፍህንና አንድነትህን አጠናክረህ እንድትቀጥልበት በማስታወስ የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ
ንቅናቄ / ትህዴን / በሁሉም አቅጣጫ የምታደርገው ትግል ከጎንህ ሆኖ
ከእሱ የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግልህ በዚህ አጋጣሚ ያረጋግጥልሃል።
በታህሳስ 1 /2008 ዓ/ም በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ በጀምዓት ሶላት በማድረግ
ላይ በነበሩ ንፁሃን የእስላምና ሃይማኖት ተከታዮች በሆኑ ወገኖቻችን
ላይ ለተፈጠረው የቦምብ መፈንዳትና ያስከተለው ከባድና ቀላል ጉዳትም፣ ጠንቁ ፀረ ህዝብ ከሆነው ገዢው የኢህአዴግ ስርአት ቢሆንም
እንኳን በንፁሃን ወገኖቻችን የዚህ አይነት የሚያሳዝን ፍፃሜ እንዳይደገምና ለድርጊቱም የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ / ትህዴን/ ድርጅት በጥብቅ ይኮንነዋል።
የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ / ትህዴን/
ታህሳስ 2008 ዓ/ም