Saturday, November 24, 2012

በአፋር ክልል የአፋምቦ ወረዳ የመስተዳድር አባላት የኢህአደግ ስርዓት የሚከተለውን ብልሹ አሰራር በመቋወማቸው ምክንያት በአሳይታ ከተማ በሚገኝ አንድ እስር ቤት መታሰራቸው ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣













በደረሰን ዘገባ መሰረት የክልሉ ህዝብ የኢህአደግ መንግስት የሚከተለውን ብልሹ አሰራር ሁሌ እንደተቃወመ ቢሆንም ፀረ-ዴሞክራሲው ስርዓት ይቃወሙኛል የሚላቸውን በማሰር ፤ በማስፈራራትና ከስራ በማባረር የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል የተልያዩ ሙከራዎችን ሲያደርግ ቆይቷል ፣ በአፋምቦ ወረዳ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍና ስቃይ መሸከም ያቃታቸው የወረዳዋ ዋና አስተዳዳሪና ምክትል አስተዳዳሪን ጨምሮ 15 የወረዳዉ መስተዳድር አካላት መንግስት በህዝቡ ላይ እያደርሰ ያለውን ግፍ በማውገዝ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቋውሞ በይፋ ገልጸዋል ፣ በአሁኑ ግዜ ግለሰቦቹ ተቃውማቸውን በመግለጻቸው ምክንያት ከሃላፊነታቸውና ከስራቸው ተነስተው ያለ ፍርድ አሳይታ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ በእስር ላይ ይገኛሉ፣
ይህ በእንዲህ እያለ የቢዱ ወረዳ የመስተዳድር አካላት የሆኑ 26 የወረዳ ሽማምንቶችን ጨምሮ 17 የአከባቢው የአገር ሽማግሌዎች አሳይታ በሚገኘው እስር ቤት ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን በክልሉ ዞን 2 የበራሕለይ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ዑስማን ዓሊን ደግሞ ከበላይ አለቆችህ የተሰጠህን ትእዛዝ አልፈጸምክም በሚል ምክንያት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል፣
የኢህአደግ ስርዓት በክልሉ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ ስዩም አወል በተባለ የክልሉ የፍትህና ጸጥታ ዋና ሃላፊ በኩል ሲሆን ግለሰቡ ስርዓቱን አይደግፉም የሚላቸውን በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ጽ/ቤቶች ተመድበው በሃላፊነትና በተራ ሰራተኝነት ሲያገለግሉ የነበሩ በርካታ ዜጎችን በማባረር በራሱ ቤተ-ዘመድ ከወዲሁ እንዲሞሉ ማድረጉን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣