Wednesday, January 23, 2013

በጡንቻው የሚያምነው አምባገነኑ የኢህአደግ መንግስት የጦር መሳሪያዎችን ወደ ትግራይ አከባቢ በማጓጓዝ ላይ ነው፣




በደረሰን ዘገባ መሰረት በርካታ ከባድና ቀላል የጦር መሳሪያዎች በትላልቅ መኪናዎች ተጭኖ ከአ/አበባ ወደ ትግራይ ተጓግዞ በሽረ አከባቢ በለስ በተባለ ልዩ ቦታ እየተሰባሰበ መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል፣
ሁኔታው በሰራዊቱ ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባትና እርስ በርስ መገዳደል ስጋት ውስጥ የገባው የኢህአደግ መንግስት ተቃዋሚዎችን ለመምታት በሚል የሰራዊቱን አስተሳሰብ ለመጠምዘዝ የሚያደርገው ከንቱ ሙከራ ነው ሲሉ የስርዓቱ የሰራዊት አባላት ይናገራሉ፣
በተመሳሳይ ሁኔታውን በሽረ ከሚታየው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር ያያዙት የሽረ አከባቢ ኗሪዎች መንግስት የፈለገውን የጦር መሳሪያ በአከባቢው በገፍ ቢያሰባስብም የአንድን ህዝብ ተቃውሞና ቁጣ በጦር መሳሪያ ማቆም እንደማይቻል ተገንዝቦ  ከወዲሁ ስልጣኑን በፈቃደኝነቱ ለማስረከብ ካልተዘጋጀ አንድ ቀን በህዝባዊ ትግል መወገዱ እንደማይቀርለት ከታሪክ መማር ይገባዋል ሲሉ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አንጸባርቀዋል፣