ጸረ-ዴሞክራሲው የኢህአደግ መንግስት ኢፍትሃዊ የዩስሙላ ምርጫ በማካሄድ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል
ህጻናትን “ለምርጫ ብልህ ሁን “ የሚል ጽሁፍ ያለበትን ቲ-ሽርት በማደልና እንዲለብሱት በማድረግ ህዝቡን ለመቀስቀስ የተለያዩ ሙከራዎችን
በማድረግ ላይ ነው ፣
በተመሳሳይ አምባገነኑ የኢህአደግ ስርዓት የሸራሮ ከተማ ህዝብን እለታዊ ስራውን እንዳይሰራ በተለያዩ ስብሰባዎች
ወጥሮ በመያዝና ከፍተኛ ጫና በማድረግ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ በማስገደድ ላይ መሆኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣
የፊታችን ሚያዝያ 2005 ዓ/ም ሊደረግ የታሰበው ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች ሁሉ በከፋ መልኩ በህዝቡ ላይ
ገና ከወዲሁ የተለያዩ ጫናዎች በማድረግ እንደተለመደው ህዝቡ ድምጹን ሰጥቶኛል ለማለት መንግስት በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ
የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣