የክልሉ የጤና ቢሮና የመስተዳድር አካላት ነጋ ጠባ በአሃዝ እየጠቀሱ የክልሉ ህዝብ በጤና ፓከጅ እንደታቀፈ
፤ ጤንነቱ እንደተጠበቀ አስመስለው ሲናገሩ የሚሰሙ ቢሆንም በአንጻሩ በክልሉ የሚገኙ የ46 ወረዳዎች የጤና ኬላ ሃላፊዎችና ምክትሎቻቸው
የክልሉ ህዝብ በጤና አጠባበቅ ዙርያ ግንዛቤው ከፍ እንዲል አለመደረጉን መግለጻቸው ከስብሰባው ተሳታፊዎች የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
ስብሰባው አባዲ የተባለ የሚገኝበት በአምስት የክልሉ የጤና ቢሮ አባላት የሚመራ ሆኖ በፍሰሃ ሆቴልና በተስፋይ
ሆቴል ለሁለት ተከፍሎ የተካሄደ ሲሆን በጤናው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን እያነሱ ከመነጋገር ያለፈ ከስብሰባው የሚገኝ ተጨባጭ መፍትሄ
እንደማይኖር ይነገራል።
በመላ አገሪቱ የመድሃኒት እጥረት እንዳለ የሚታወቅ ሆኖ በትግራይ ከልል ደግሞ ችግሩ በከፋ ሁኔታ የሚገለጽና
ህዝቡም የሚማረርበት ጉዳይ መሆኑን በክልሉ የሚገኙ የጤና ኬላ ሃላፊዎች መግለጻቸው ቷውቋል።
በስብሰባው የተነሱ ችግሮች ስብሰባው እንዳለቀ ወዲያውኑ እንደሚረሱና ዞር ብሎ የሚያይ የክልል ባለስልጣን
እንደሌለ ከዚህ በፊት ከተደረጉት ተመሳሳይ ስብሰባዎች መገንዘብ ይቻላል ሲሉ ከየወረዳው የተወከሉ የጤና ባለሞያዎች መናገራቸው የደረሰን
ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።