በባህርዳር ከተማ በሚገኝ አንድ የእጣንና ሙጫ ፋብሪካ በደረሰው ምክንያቱ ያልታወቀ ድንገተኛ ፍንዳታ በርካታ
የፋብሪካው ጥሬ እቃዎችንና ያለቀላቸው የፋብሪካው ምርቶችን ተከማችተውበት የነበረ አንድ ትልቅ መጋዝን ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል፣ ሁኔታው
በፋብሪካው ሰራተኞችና በአከባቢው ኗሪዎች ላይ ድንጋጤ መፍጠሩን ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
ከፋብሪካው ቃጠሎና በከተማዋ አስራ አራት ሰዎችን ገድሎ እራሱን ካጠፋው አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ጋር
በተያያዘ ሁኔታ 22 የፌደራል ፖሊስ አባላት ጉንበት 12,2005 ዓ/ም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ለማወቅ ተችሏል።
በሌላ በኩል በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ የተሰማሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት
በህብረተሰቡ ውስጥ ገብተው ጫና በመፍጠራቸው የአከባቢው ኗሪ እለታዊ ህይወቱን መምራት መቸገሩን ቷውቋል።