በደረሰን ዘገባ መሰረት ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በመዋጮ በተሰበሰበው ገንዘብ ለፕሮጀክቱ ስራ ማስፈጸሚያ
ተብሎ የተያዘው ስሚንቶና ተንዲኖ ስራውን እንዲመሩ በአከባቢው በተመደቡ የስራ አመራሮች እየተዘረፈ በኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥሩ 00567
አማራ ቮልቮ የተጫነ ተንዲኖና በኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥሩ 00908 አማራ ተሽከርካሪ የተጫነ ስሚንቶ ከግድቡ ወደ ባህርዳር ከተማ እንዲጓጓዝ
ከተደረገ ብሁዋላ ኗሪነታቸው በክተማዋ ለሆኑ አቶ መንግስቱ የተባሉ ባለሃብት እንደሸጡላቸው ቷውቋል።
ሁኔታውን የደረሱበት የከተማዋ ኗሪ የሆኑ አንዳን ተቆርቋሪ ዜጎች መንግስት ከህዝብ ለግድቡ ማሰሪያ ተብሎ
በየግዜው የሚወጣውን ገንዘብ በትክክል ስራ ላይ መዋሉን ማስረዳት አለበት ፣በህዝቡ እየተዋጣ ያለው ገንዘብ ለግለሰቦች ጥቅም እየዋለ
ነው ፣ ዝርፊያው እንዲህ ከቀጠለ የግድቡ በተያዘለት ግዜ መጠናቀቅ አጠያያቂ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ
ጨምሮ ያስረዳል።