Friday, May 10, 2013

በአማራና ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የእርሻ መሬታቸው በመንግስት ተወስዶባቸው ከቀያቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ላይ በደል እየደረሰ ነው።



በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ማንዲራ ዞን ፣ በታዊ ልዩ ወረዳ የሚገኙ የሰዋስት ፣ መንደር 5 ፣ መንደር 9 ና በሌሎች አከባቢዎች ለስኳር አገዳ ልማት እንዲውል በሚል አርሶ አደሩን በማፈናቀል ያለምንም ካሳና ተለዋጭ መሬት ለጣና በለስ ፕሮጀችት እንዲሰጥ በመደረጉ ከቀያቸው የተፈናቀሉት ገበሬዎች በችግር ላይ ይገኛሉ ።
በአውላላ ሜዳ ላይ የተጣሉት የአከባቢው ኗሪዎች መፍትሄ ለማግኘት ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበው ሰሚ አላገኙም። የአከባቢው የመንግስት ባለስልጣናት የህዝቡን ጥያቄ በአግባቡ በመቀበል መልስ መስጠት ሲገባቸው ወደ አከባቢው የፌደራል ፖሊስ ሃይል በማሰማራት ሰበብ እየፈጠሩ ኗሪውን ማዋከብና መቀጥቀጥ ቀጥለውበታል።
በተመሳሳይ ኗሪነታቸው በአማራ ክልል ፣ አዊ ዞን ፣ በጃዊ ወረዳ ስር የሚገኙ አምስት ቀበሌዎች የሆኑ አርሶ አደሮች አከባቢው ለስራ ተፈልጓል በሚል ምክንያት ከቀያቸው በመንግስት እንዲፈናቀሉ ከተደረገ ብሁዋላ በተለምዶ አንዱ-ቁራ በመላል በሚጠራው አከባቢ ሜዳ ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል።
   የኢህአዴግ ስርዓት የአርሶ አደሮችን መፈናቀል አከባቢው ለጣና በለስና ለስኳር ልማት ፕሮጀችት ስለተፈለገ ነው ቢልም ቅድሚያ ለሰብአዊነት በመስጠት ተፈናቃዮቹ የሚሰፍርባቸው ቦታዎችን በመለየት የውሃ ፣ የጤናና ሌሎች የማህበራዊ አገግሎቶችን አቅርቦት ማመቻቸት ሲገባው ያለ ቅድመ ሁኔታ በማፈናቀሉ በርካት ህጻናት ፣ ነብስ ጡር እናቶችና በእድሜ የገፉ ወላጆች የሚገኙባቸው የአከባቢው ኗሪዎች ለተለያዩ በሽታዎች ተዳርገው ይገኛሉ።