Friday, May 10, 2013

በፌደራል ዋና ኦዲተር ጽ/ቤት ሪፖርት መሰረት በያዝነው ዓመት በሁለት የመንግስት ሚኒስቴር መስሪያቤቶች ብቻ ከ 648 ሚልዮን ብር በላይ የፋይናንስ ብክነት መድረሱን ቷውቋል።



የፌደራል ዋና ኦዲተር ጽ/ቤት መጋቢት 17,2005 ዓ/ም ባቀረበው ዓመታዊ ሪፖርት መሰረት ለውሃ ሃብት ሚኒስቴር ከተመደበው በጀት ከ368 ሚልዮን ብር በላይ የባከነ ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴርም ከ 28 ሚልዮን 900 ብር ለተመደበለት ስራ ሳይውል መጠፋፋቱን ለማወቅ ተችለዋል።
ይህ በሚኒስቴር ደረጃ በሚንቀሳቀሱ ትላልቅ የመንግስት ጽ/ቤቶች የባከነ ገንዘብ ለተለያዩ ሃገራዊ ፕሮግራሞችን ማስፈጸሚያ ተብሎ ከመንግስት ከተመደበው በጀት ሌላ ጽ/ቤቶቹ ከውስጣቸው ከሚያገኙት ተጨማሪ ገቢ የተገኘ ሲሆን ህጋዊነት በሌለው ሰነድ ወጪ እየሆነ ለግለሰቦች ጥቅም ሲውል የቆየ መሆኑ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።
በዚህ የሙስና ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች በዋናነት በሚኒስትር ደረጃ የሚገኙ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሲሆኑ በስራቸው ተመድበው በሞያቸው የሚሰሩ በርካታ ግለሰቦችም ይገኙበታል።