በአቶ ጥላሁን በርሀ የተመራውና ከጉንበት 2-4,2005 ዓ/ም ለሦስት ቀናት የተካሄደው የህወሓት አባላት
ስብሰባ በአጀንድነት የቀረቡ።- ኗሪው ህዝብ በመንግስት ተተምኖ የሚቀርብለትን ግብር ለምን ያለማንገራገር አይከፍልም? የሚል ሆኖ
አባሉ የአሰራር ለውጥ እንደሌለ አውቆ መላው ህዝብ በተለይም ደግሞ ነጋዴው ባለሃብት ከመቃወም ይልቅ የተጠየቀውን ግብር እንዲከፍል
ለማድረግ የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም ህዝቡን መቀስቀስ ይጠበቅበታል በማለት በተሰብሳቢው ላይ ጫና ለማድረግ ሞኩራል።
ነገር ግን ተሰብሳቢዎቹ የህዝቡ ፍላጎት ፍትህንና ነጻነትን መረጋገጥ እንደሆነና ግብር የመሰብሰብ ጉዳይም
በሞያው ለተሰማሩ የመንግስት ባልሞያዎች የሚተው እንጂ እኛን የሚመለከት ጉዳይ አይደለም በማለት የቀረበውን ሃሳብ በአንድ ድምጽ
ውድቅ አድርገውታል።
ሌላው በዚህ ስብሰባ በአጀንዳነት የቀረበው ጉዳይ ትህዴን ከመቸውም ግዜ በላይ ህዝባዊ ተቀባይነትን እያገኘ
መምጣቱን ለዚሁ ዋና ማረጋገጫም በከተማዋ ካሉት አባሎቹ የሚደርሰውን በከተማዋ የተፈጸመ ማንኛውንም ነገር ሳይውል ሳያድር ተቀብሎ
በዜና መዘገቡ ነው የሚል ሆኖ ፣ ይህ ሊሆን የቻለው በአባላት ድክመት መሆኑን አውቃችሁ በትህዴንን እየተደረገ ያለውን ሰፊ እንቅስቃሴ
ለመቆጣጠር በከተማዋ መግቢያና መውጫ መንገዶችን በቅርብ መከታተልና የከተማዋ ኗሪ ህዝብም በንቃት አከባቢውን እንዲጠብቅ በማድረግ
ከናንተ ብዙ እንጠብቃለን በማለት አሳስባል ፣ ነገር ግን ተሰብሳቢዎቹ የትህዴን እንቅስቃሴን መከታተል የመከላከያ ሰራዊትን የሚመለከት
እንጂ ሲቪል ኗሪን የሚመለከት ጉዳይ አይደለም በማለት በአንድ ድምጽ በመቃወማቸው ስብሰባው ያለ ፍሬ መበተኑን ለማወቅ ተችሏል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዓዲ-ጸጸርና ቢያራ የሚገኙ እረኞች ከትህዴን ጋር ግንኝነት አላችሁ በሚል ተይዘው
በማይታወቅ እስር ቤት ታስረው እየተቀጠቀጡ መሆናቸውንና እንደዚሁም የ 33ኛ ክ/ጦር 2ኛ ሬጅመንት ማእርግ ይገባናል ብለው የጠየቁ
በርካታ መኮኑኖች ከትህዴን ጋር ግንንነት አላቸው በሚል ሰበብ የታሰሩ ሲሆን ፥ ከታሰሩት ወታደሮች መካከል ፷/አለቃ ታረቀ የተባለ
ጉንበት 3,2005 ዓ/ም በለሊት አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ እንደወሰዱት የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።