Saturday, May 25, 2013

በመገንባት ላይ ባለው የህዳሴው ግድብ ተመድቦ በስራ ላይ የሚገኘው ኢንጂነር ቪርዶ ስራን አጓትተሃል በሚል ከስራው እስከ ማባረር የሚደርስ ማስጠንቀቅያ ተሰጠው፣፣



ጣሊያናዊው ኢንጂነር ቪርዶ የሳሊኒ ኮንስትራክሽን ዋና ማሃንዲስ ሲሆን የአባይ ወንዝን የመቀልበስ ስራን አጓትታሃል በሚል የተወቀሰ ሲሆን በአንድ ሳምንት ውስጥ ወንዙን መቀልበስ ካልቻለም ከስራው እንደሚባረር ማስጠንቀቅያ መሰጠቱን ለማወቅ ተችለዋል፣፣
የተሰጠውን ማስጠንቀቅያ ተከትሎ ኢንጂነሩ በይድረስ ይድረስ ስራ ወንዙን መቀልበስ ቢችልም ወንዙን የመቀልበስ ስራ ጥራት ጋር በተያያዘ ሰራተኞቹ ስጋታቸውን እየገለጹ ሲሆን ወቅቱ የክረምት መግቢያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የወንዙ ውሃ ሙላት ስለሚጨምር የመቀልበሱን ስራ በክረምት ወራት የሚኖረውን ከፍተኛ የውሃ ግፊት መቋቋም በሚችል ደረጃ ግዜ ወስዶ መሰራት ይገባ ነበር ሲሉም አክለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ፣፣
በሌላ በኩል ከቤንሻንጉል ጉምዝ ከተፈናቀሉ ብሁዋላ ዳግም ወደ ቦታቸው የተመለሱት የአማራ ብሄር ተወላጆች በአከባቢው ከሚኖሩ የቤንሻንጉል ተወላጆች ጋር አሁንም በሚፈጠሩ የርስ በርስ ግጭቶች ምክንያት ንብረት እየተዘረፈ ሲሆን ሰፋሪዎቹ ለሚመለከታቸው የክልሉ ባለስልጣናት አቤት ቢሉም የሚሰማቸው እንዳላገኙ የደርሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣፣