በናዕዴር ዓድየት ወረዳ የንጹህ የመጠጥ ውሃ ፤ የትራንስፖርትና የመብራት አገልግሎቶች የሉም፣ የጤና አገልግሎትንም
ቢሆን በአከባቢው የጤና ጣብያ ህንጻ ቢኖርም በቂ መድሃኒትና ባለሞያ ስለሌለው በወሊድ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን
ቷውቋል።
የወረዳዋ ኗሪ ህዝብ ለብዙ ዓመታት በተጠቀሱት የማህበራዊ አገልግሎት ችግሮች ሲሰቃይ የቆዩ ሲሆን በአሁኑ
ጊዜ ችግሩ ተባብሶ መሸከም በማይችሉበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ኗሪው ከመካከሉ ይወኩልኛል የሚላቸውን ሰዎች በመምረጥ ችግሩን ለዞንና
ክልል ባለስልጣናት አቅርቧል።
ነገር ግን የክልሉ ባለስልጣናት በክልሉ የማህበራዊ አገልግሎት አቅርቦትን ችግር እንደተፈታና ችግር አለበት
የሚባል አከባቢም ካለ በግልጽ ችግሩን ያቅርብ ለመፍታት ዝግጁ ነን በማለት በሚቆጣጠሩት ሚድያ እየተናገሩ ባለበት በአሁኑ ወቅት
በናዕዴር ዓድየት ወረዳ ኗሪዎች የቀረቡትን ችግሮች ከመፍታት ይልቅ በወረዳዋ የሚኖሩ ነባር ታጋዮችን ህዝቡን አነሳስታችሃል በማለት
ሲያዋክባቸው ይታያሉ።