በደረሰን ዘገባ መሰረት በዚሁ ክልል ከብዙ ዓመታት በፊት ከተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች መጥተው በክልሉ
የሰፈሩ በርካታ ብሄር ብሄረሰቦች የሚገኙ ሲሆን ፥ የኢህአዴግ ስርዓት በሚከተለው የለያይተህ ግዛ ፖሊሲ በመሃከላቸው ልዩነቶችን
በመፍጠር ለብዙ ዓመታት ተስማምተው ሲኖሩ የነበሩ የአከባቢው ኗሪዎች እርስ በርሷቸው እንዲጋጩ እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በያዝነው ሳምንት በአከባቢው በሚገኙ ብሄረሰቦች መካከል ከፍተኛ ግጭት በመቀስቀሱ ምክንያት የአከባቢው ኗሪ
ስጋት ላይ የወደቀ ሲሆን ለደህንነቱ ዋስትና ያጣ አብዛኛው ኗሪ መኖሪያ ቤቱን እየተወ በየበረሃው ተደብቆ የሚውልበትና የሚያድርበት
ሁኔታ እንዳለ ታውቋል።
በተቀሰቀሰው ግጭት ከተገደሉት ሰዎች አንዱ ፤ አቶ ጌታቸው አንቁሬ የተባሉ የመንግስት ሰራተኛ የብሄረ ሃድያ
ተወላጅ ይገኙበታል፣ ገዳዮቹ የሚታወቁ ሆኖ የማቹ ቤተሰብ ተይዘው ወደ ህግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል ፣ ነገር ግን የክልሉ ፖሊስ ወንጀሎኞችን
ለጊዜው በማሰር ስለለቀቃቸው ገዳዮቹ የልብ ልብ ተሰምታቸው የማቹን ቤትሰቦች ክስ እንዳይመሰርቱባቸው ማስፈራራት መጀመራቸውን የደረሰን
ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።