ከስምንት ዓመታት የዜጎች ህገ-መንግስታዊ መብት እገዳ ብሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ህጋዊ ፈቃድ አግኝቶ በቅርቡ
በአ/አበባ ከተማ በተካሄደው በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ኢህአዴግ ከገመተው ውጭ ስለሆነበትና በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ
በመሳተፉ ሁኔታው የስርዓቱን ህልውና የሚፈታተን ነው በሚል ስሌት በማየት ሰበብ እየፈጠሩ የሰላማዊ ሰልፉን አደራጆችንና ተሳታፊዎችን
በማሰርና በማስፈራራት ለቀጣይ እንዳይደገም የሚያደርግ አሰራር እየተከተሉ መሆኑን ከከተማዋ የወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
በደረስን ዘገባ መሰረት የኢህአዴግ ስርዓት የሰላማዊ ሰልፉን አስተባባሪዎችን በመከታተል ላይ ሲሆን እስካሁን
ድረስ ታዋቂ ሰዎች የሚገኙባቸው በርካታ ዜጎች በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ያለምን ፍርድ በየእስርቤቱ ቷጉረው በስቃይ ላይ
እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።