የሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ኗሪ ህዝብ በከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንግድ እንዲሰራ ሁሉም እንደየ አቅሙ በማዋጣት
በርካታ ገንዘብ ቢያሰባሰብም እስካሁን ድረስ አንድም በከተማዋ ውስጥ የተገነባ የውስጥ ለውስጥ መንገድ የለም ። ህዝቡ የተሰባሰበው
ገንዘብ የት ገባ የሚል ጥያቄ አስነስታል። በተለይም በያዝነው ሳምንት በከተማዋ በተደረገ ስብሰባ ኗሪው መልስ እንዲሰጠው የከተማዋን
የመስተዳድር አካላትን ወጥሮ ይዛል ።
በከተማዋ
ከንቲባ አቶ ፍስሃ ውበትና የዞን አስተዳዳር አቶ ምክኤለ አብረሃ የተመራ ስብሰባ በዚሁ ሳምንት የተካሄደ ሲሆን በተሳታፊዎቹ ለከተማዋ
የውስጥ ለውስጥ መንገድ ማሰሪያ በሚል የተሰባሰበው ገንዘብ የት ገባ? እስካሁን ድረስ በከተማዋ ውስጥ የተሰራ አዲስ መንገድ የለም
የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል። የከተማዋ የመስተዳድር አካላትም የባከነ ገንዘብ እንደሌለ በማስመሰል ህዝቡን ለማሳመን ያደረጉት ሙከራ
በከተማዋ ኗሪ ዘንድ ተቀባይነት እንዳላገኙ ታውቋል።