Tuesday, June 18, 2013

መኖሪያ ቤታቸው የፈረሰባቸው የሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ኗሪዎች ሜዳ ላይ ወድቀን ዝናብ ፤ ጸሓይና ብርድ አተፈራረቀብን ነው ይላሉ።



በደረሰን ዘገባ መሰረት በከተማዋ 01 ቀበሌ የሚገኙ 68 መኖሪያ ቤቶች በሰኔ 7,2005 ዓ/ም በከተማዋ በሚገኙ የጸረ-ዴሞክራሲው ስርዓት ባለስልጣናት ትእዛዝ ያለ ምንም ካሳና ተለዋጭ መሬት ቤታቸውን ያጡ በርካታ ዜጎች ወቅቱ የክረምት ወራት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለዝናብ ፤ ጸሃይና ብርድ ተጋልጠው በችግር ላይ የገኛሉ።
በየጎዳናው ወድቀው ያሉት እመጫቶች ፤ ነብስ ጡሮች ፤ ህጻናትና ሽማግሌዎች የሚገኙባቸው በርካታ ዜጎች ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ ሲሆን ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም መፍትሄ እንዳልተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል።
ከጉንበት ወር 2005 ዓ/ም አጋማሽ ጀምሮ በዚች ከተማ በመንግስት ሃይሎች ቤታቸው የፈረሰባቸው በርካታ ዜጎች በየጎዳናው ወድቀው ለተለያዩ በሽታዎች መጋለጣቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው።