Wednesday, December 11, 2013

በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ ኣካባቢ እሳት ኣደጋ በመከሰቱ ከኣንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እንደወደመ ምንጮች ከቦታው ኣስታወቁ፣




በደረሰን መረጃ መሰረት። በየቀኑ ስፊ የንግድ ልውውጥ የሚካሄድበትና በርከት ያሉ ነጋዴዎች የሚንቀሳቀሱበት የመርካቶ ገበያ። ህዳር 25/ 2006 ዓ.ም ባጋጠመው የእሳት ኣደጋ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እንደወደመና። በወቅቱ የእሳት አደጋ መከላከያ ድርጅት አፋጣኝ እርዳታ እንዲወስድ ጥሪ  ቢደረግለትም። አልታዘዝንም በሚል ሰንካላ ምክንያት አደጋ ወደ  ደርሰበት ቦታ ሊሄዱ ባለመቻላቸው። የህዝብና የሃገር ሃብት እንዲወድም ምክያት ሆነዋል ሲል አስረድተዋል፣
     እነዚህ በእሳቱ አደጋ ተጎጂ የሆኑ ዜጎቻችን። የእሳት አደጋው ሰፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት። ለሚመለከታቸው ኣካላት ቢያስታውቁም። የተሰጠው ህዝባዊ ተልእኮ በተገቢው መንገድ ያልተዋጣው የእሳት መከላለያ ድርጅት ለጉዳዩ አፋጣኝ መልስ ባለመስጠቱና። ኣጠቃላይ የበላይ አስተዳደሩ በወለደው ችግር ምክንያት ይህን ሁሉ ኪሳራ ያጋጠመው በሚል ምክንያት። መንግስት ካሳ እንዲከፍላቸው ላቀረቡት ጥያቄ እስካሁን ተገቢውን መልስ እንዳልተሰጡ ለማወቅ ተችለዋል፣
     በተመሳሳይ መንገድ በመቀሌ ከተማ መደብር አምስትና መደብር አስራ አንድ ተብሎው በሚጠሩ ቦታዎች። ህዳር 23 እና 25/ 2006 ዓ.ም። ለረጅም ግዜ ተበላሽቶ በቆየ መሆኑን በሚታወቅ ትራንስፎርመርና ሌሎች ምክንያቶች። በተፈጠረው የእሳት ቃጠሎ። በርከት ያለ የህዝብ ንብረት እንደወደመና። የዚህ ኣደጋ ዋነኛ ምክንያትም ያካባቢው አስተዳዳሪዎች ቸለልተኝነት መሆኑ ተገልፀዋል፣
     በተለይ በህዳር 25/2006 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ በርከት ያለ የንግድ እንቅስቃሴ በሚደረግበት መደብር አስራ አንድ በተባለው ቦታ የተፈጠረው የእሳት ቃጠሎ። በቦታው ውስጥ ሆነው ከመንግስት ከሶስት መቶ ሺ እስከ አምስት መቶ ሺ ብር (300,000 – 500,000) በላይ ብድር ወስደው በተለያዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ስራዎች ተሰማርተው ሲሰሩ የቆዩ ወገኖች። ኪሳራ ውስጥ በመውደቃቸው። መንግስት የሰጠን ብድርና። እንድንከፍለው የተወሰነልን ግብር መክፈል ስለማንችል። ነፃ ይልቀቀን እያሉ መቆየታቸው ታወቀ፣