Wednesday, December 11, 2013

በሁመራ አካባቢ ራውያንና ሉጉዲ በተባሉ ቦታዎች። ፀረ ሽፍታ በመባል የሚታወቁ የስርኣቱ ፌደራል ፖሊስና ታጣቂ ምልሻዎች። ከህዝብ ንብረት እየነጠቁ ለግላቸው እያከማቹ እንዳሉ ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ፣




በምእራብ ትግራይ ዞን  ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ራውያን ሉጉዲና ሌሎች ኣካባቢዎች የሚገኙ። በየቀኑ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን እየተመላለሱ የሚሰሩ ነጋዴዎች። ፀረ ህዝብ የስርኣቱ የፌደራል ፖሊስና ታጣቂ ሚልሻዎች በመሆን። ከነጋዴዎቹ እጅ የተያዘው ንብረት በኮንትረባንድ የመጣ  ነው በሚል ምክንያት። እቃው ወደ ህጋዊ ቦታ ሳይወስዱ ማይ ካድራ ወደሚገኘው ሃለቃ ተክላይ የተባለው የስርኣቱ ተባባሪ ነጋዴ ወስደው ኣየር በኣየር በመሸጥና ከበላይ ሃላፊዎቻቸው በመስማማት ለግል ጥቅማቸው እንደሚያውሉት የደረሰን መረጃ ኣስታወቀ፣
     ከዞኑ ሳንወጣ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮለጆች ተምረው ስራ ያጡ በርከት ያሉ ወጣቶች። በረኸት በተባለው ኣካባቢ በጉልበት ስራ ተሰማርተው እየስሩ ቢቆዩም። የህወሓት ኢህአዴግ ስርአት ባሰማራቸው የፀጥታ ሃይሎችና ካድሬዎች ህዳር 12/2006 ዓ.ም። ከተቃዋሚ ድርጅቶች እየተገናኛቹህ መረጃና ሌሎች እገዛ እያረጋቹህ ነው በሚል ተጨባጭነት የሌለው ምክንያት። ከቦታው በአስቸካይ እንዲለቁ እንዳስጠነቀቅዋቸውና። ከዛን እለት ጀምሮ ወጣቶቹ በፀጥታ ሃይሎች እየታፈኑ መሆናቸው ታወቀ፣
    በስርኣቱ የፀጥታ ሃይሎች ከታፈኑና እስካሁን የት እንደደረሱ ከማይታወቁ ወገኖች ስም ለመጥቀስ።
-- ተክሊት ፀጋይ ከመረብ ለኸ፤  ከበደ መሃመድ ከወሎ ኣካባቢዎች የሄዱ ሁለቱም በቀን ሰራተኝነት የጉልበት ስራ ሲሰሩ የነበሩ።
-- ምህረተኣብ ኪሮስ፤ ገሬ ካህሳይና ኣግደው ሽሙየ። በሰፈራ ምክንያት ወደ ሩዋሳ የመጡ። ቀደም ሲል በስርኣቱ ታጣቂዎች ማስፈራርያ እየደረሳቸው የቆዩንና። ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ እስካሁን የት እንደደረሱ ያልታወቁ ወገኖች መሆናቸውን መረጃው አክሎ አስታውቀዋል፣