Saturday, January 4, 2014

በሰራነው የኣገልግሎት ዘመን እድገት ልናገኝ ኣልቻልንም ያሉ ኣስተማሪዎች የሚሰማ ኣካል ባለ ማግኘታቸው የነበራቸው ስራ እየለቀቁ እንደሚገኙ ታወቀ፣




በትግራይ ክልል ከኣንደኛ ደረጃ እስከ ክፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመድበው በሞያ ኣስተማሪነት ለረጅም ግዜ ሲያገለግሉ የቆዩ ዜጎች የሰሩበት የኣገልግሎት ዘመን ታይቶ የስራ እድገት የማግኘት መብታቸው ተገቢ ቢሆንም በወያኔ ኢህኣዴግ ስራኣት ብልሹ  ኣሰራር ምክንያት። ማግኘት የሚገባቸው ቦታ እንዳላገኙ ለማወቅ ተችለዋል።
    እነዚህ ሚሬታቸው እያሰሙ የሚገኙ ኣስተማሪዎች ታህሳስ 13 2006 ዓ/ም በሰጡት መረጃ መሰረት በቅርብ ሃላፊዎቻቸው የህ.ወ.ሃ.ሓ.ት ኣባላት እንዲሆኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብላቸውም እነሱ ግን ከተመደቡበት ስራ በስተቀር ሌላ በጎን የሚመጣ የስርኣቱ ፖለቲካዊ ስራ እንዲያከናውኑ ፍቃደኞች ባለ መሆናቸው የተለያዩ ኣሳማኝ ያልሆኑ ምክንያትች በመደርደር የላባቸውን ዋጋ እንዳያገኙ የስራኣቱ ካድሬዎች እንቅፋት እየሆኑባቸው እንደሆኑ መረጃው ኣስታዉቀዋል፣
    ኣስተማሪዎቹ በማስከተል የስርኣቱ እድሜ ህጋዊነት በሌለው ክራይ ሰብሳቢነትና ሙስና ላይ የተንጠለጠለ በመሆኑና በትምህርት ሚንስተር በኩልም እንደኣሰራርና ግዴታ ሊያገኙት የሚገባ መብት በስራኣቱ የተዛባ የፖለቲካ እመለካከት እየታየ ኣስተማሪዎቹ የስራ ነፃነት ተነፍገው የስርኣቱ የፖለቲካ መሳርያ ለመሆን እየተገደዱ በመሆናቸው የሰብኣዊ መብት ተቆርቃሪ ድርጅቶችና ህዝቡን ለዚህ መጥፎ ስራ  እንዲቃወሞው ጥርያቸው ኣቅርበዋል፣  
      በትግራይ ክልል የሰራትኞች እድገት ሃላፊ  ኣቶ ሰይፈ ኣንበስ ከስራኣቱ ጎን ቁሞ የሰራተኞቹ መብት ወደ ጎን በመተው ከስርኣቱ ባለስልጣኖች እየተመካከረ የራሱን ሃብት በማከማቸት ስራ ላይ ተጠመዶ እንደሚገኝና ከኣስተማሪዎቹ የተሰበሰበ ገንዘብ ይዞ ለመጥፋት ሲሞክር ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ተይዞ በቁጥጥር ስር ዉሎ ሲያበቃ ያለ ምንም ጥያቄ ነጻ እንደተለቀቀ ለማወቅ ተችለዋል።