Saturday, January 4, 2014

የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች በህጋዊ መንገድ የተሰጣቸው መሬት ሃላፍነትና ህጋዊ መንገድ በጎደለው መንገድ መንግስት እየወሰደው ነው ሲሉ ብሶታቸውን ኣሰሙ፣




በከተማዋ ኣስተዳደር ለረጅም ግዜ ተሰጣቶዋቸው የቆየ መሬት ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ በስልጣን የሚገኝ መንግስት በተላላኪዎቹ እያደረገ ከ ታህሳስ 2/ 2006 ዓ/ም ጀምሮ እየወሰደው ሲሆን ከባለ ስልጣናት ትስስር ያላቸው ዜጎች  ለኣንድ ካሬ ሜትር 1800 ብር ካሳ ሲሰጣቸው ለችግሮኞቹና ባለ ስልጣን ዘመድ ለሌላቸው ዎጎኖች ግን 250 ብር ብቻ እየሰጥዋቸው ኣንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል፣
   እነዚህ በስራኣቱ ወገናዊነት የተጠናወተው ኣሰራር  የተበደሉ ወገኖች መሬታችንና ቤታችን ነጥቃቹህ በባዶ ሜዳ መጣላቹህን ሳያበቃ ለባለ መሬት ካሳ ኣንዲሰጥ ተብሎ ከሃገር ሃብት ለመጣው ገንዘብ ለሁላችን ያገሪትዋ ዜጎች በእኩል የሚመለከተን በመሆኑ፤  የናንተን ደጋፊዎች እንደወሰዱት ልንሰጥ ይገባል የሚል ጥያቄ ቢያቅርቡም፤ ከሚመለከተው ኣካል ኣወንታዊ መፍትሔ እንዳልተሰጣቸው መረጃው ኣክሎ ኣስገንዝበዋል።