Sunday, January 5, 2014

በኣገራችን ውስጥ የሚንቀሳቀሰው መድረክ በመባል የሚታወቀው ተቃዋሚ ድርጅት ኣላማዎቹ ለህዝብ ለማሳወቅ በማለት የሚድያ ስርጭት ይፈቀድልኝ ብሎ ላቀረበው ጥያቄ በኢህኣዴግ ባለ ስልጣኖች ኣሉታዊ ምላሽ እንደተሰጠው ተገለፀ፣




ይህው መድረክ የተባለው ተቃዋሚ ድርጅት በህዳር 14/2006 ኣ/ም ውስጣዊ ኣደረጃጀቱ ማስተካከል እንዳደረገና ለዚሁ ኣዲስ የተቀናጀ እሰራሩ በመገናኛ ብዙሃን ተጠቅሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለመግለፅ ህጋዊ በሆነ መንገድ  ለባለስልጣኖቹ ጥያቄ ቢያቀርብም ተቀባይነት ኣንዳላገኘና ይባስ ብሎ የድርጅቱ ኣመራር ለሆነው ኣቶ ሃይሉ ሻውል ባጭበርባሪነት ፈርጆው እስር ቤት ውስጥ ስላስገቡት የድርጅቱ ኣባሎች ብሶታቸው እያሰሙ መሆናቸው ያገኘነው መረጃ ኣስታወቀ፣
    መረጃው ጨምሮ የወያኔ ኢህኣዴግ ባለስልጣኖች የፕሬስ ነፃነት እንዳለ ለማስመሰል በመገናኛ ብዙሃናቸው የሚያሰራጩት ከሃቅ የራቀ ኡነታ ለፖለቲካዊ መሳርያነት እንድያገለግላቸውና ከሃብታም ኣገሮች የሚያገኙት እርዳታ እንዳይቛረጥ በማሰብ ብቻ የሚጠቀሙበት ብልሃት እንጂ በተግባር ላይ እንደማይጠቀሙበት መረጃው ኣስታውቀዋል፣
     እንደሚታወቀው በተለያዩ ያገራችን ኣካባቢዎች የሚገኙ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ድርጅቶች በላያቸው ላይ ግፍ እየወረደባቸው እንዳለና ከነዛም ውስጥ ኣረና ትግራይ የተባለው ድርጅት ትግራይ ውስጥ ባሉ ኣባሎቹ ላይ ኣንዳች የፈፀሙት ወንጀል እንደሌላቸው እየታወቀ በግፍ እየታሰሩ፤ እየተደበደቡና ከስራ እየተባረሩ ከመሆናቸው በላይ ለሚከፍትዋቸው ፅ/ቤትም የቤት ኣካራዮችን በማስፈረት እንዲዘጋ እደሚያደርጉ ባለፈው የዜና እወጃችን መግለፃችን ይታወቃል፣