እነዚህ ወጣቱን ለማደናገር ተብሎው ከበላይ
ባለስልጣኖችና ታማኝ የስራኣቱ ካድሬዎች የተውጣጡ ኣካላት በሁመራ ከተማ የሚገኝ ወጣት ሃይል የተለያዩ የማይተገበሩ ቃል በመግባትና
ወደ ፖሊስ ሰራዊት እንዲመለመሉ ለማስቻል ያደረጉት እንቅስቃሴ። እንዳልተሳካላቸው የደረሰን መረጃ እስታውቀዋል፣
መረጃው በማስከተል በከተማው ውስጥ ሲንቀሳቀሱ
ይሁን በተለያየ ስራ ላይ ተሰማርተው ለነበሩ ነዋሪ ይሁን ኣዲስ መጤ እንግዳ ሳይለዩ በታህሳስ 20 እና 21/2006 ኣ/ም ለሁለት
ቀን ባካሄዱት ተደጋጋሚ ስብሰባ ማንነታቸው ለማይታወቁ ወጣትም ጭምር ወደ ፖሊስ ኣንዲመለመሉ መንግስት መፍቀዱንና በማሰልጠኛው ውስጥ
ከገቡም በኅላም፤ የተለያየ የሞያ ስልጠና ሊሰጣቸው እንደሆነ ላቀረቡት የማታለያ ቃል ተሰብሳቢው ህዝብ የገባችሁትን ቃል ለኣመታት
ያሰለቸን ነው በማለት እንደተቃወማቸው ለማወቅ ተችለዋል፣
ከሁመራ ከተማ ሳንወጣ በከተማው ውስጥ
ላለው የተበላሸ የእስፋልት መንገድ ለመሰራት የመጣው የቻይና ኩባንያ በተገቢው መንገድ መስራት ባለመቻሉ ምክንያት ከባለስልጣኖቹ
ጋር ንትርክ ውስጥ መግባቱ ለማወቅ ተችለዋል፣
የመንገድ እስፋልቱን በኮንትራት የተረከበው
ይሀው የቻይናው ኩባንያ በውሉ መሰረት ሰርቶ ሊያስረክብ ከተቃረበ በሃላ፤ በባለሞያዎች ተገምግሞ ጥራት እንደሌለው በመረጋገጡ ምክንያትና
የከተማው ኣስተዳዳሪዎችም ስጋት ውስጥ ገብተው እንረከብም ባሉበት ባሁኑ ሰኣት ኩባንያው ግን በገባሁት ውል መሰረት ሰርቼ ጨርሻሎህ
የማሻሽለውና የምቀይረው የለኝም የሚል መልስ በመስጠቱ ምክንያት በመሃላቸው ውስጥ ንትርክ ተፈጥሮ እንዳለና የመንገዱ ስራም ተጠቅልሎ
እንዳይጨረስ በመሰናከሉ በመሃል ስለተቓረጠ። ባሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ሻግር ፈጥሮ እንዳለ መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣