Tuesday, January 7, 2014

በሽራሮ ከተማ ወንጀልን ለመከላከል በሚል ምክንያት በፖሊስ የተዘጋጀው መድረክ ባካባቢው ነዋሪ ህዝብ ተቀባይነት እንዳላገኘ የተገኘው መረጃ ኣመለከተ፣




በመረጃው መሰረት በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ ዞን በሸራሮ ከተማ የሚገኝ የፖሊስ ፅ/ቤት በታህሳስ 20/2006 ኣ/ም ለጠቅላላ የከተማው ህብረተሰብ ሰብስቦው ወንጀልን መከላከል በሚል ተከፈተው የስብሰባ መድረክ ከህብረተሰቡ ተቃውሞ እንደገጠመውና በመጀመርያ ደረጃ በውስጣቹህና በተለያዩ የመንግስት ፅ/ቤቶች እየታየ ያለው ብልሹ ኣሰራር በሚገባ መንገድ ገምግማቹህና ኣስተካክላቹህ ካልመጣቹህ የምትሉትን ነገር ኣንሰማችሁም በማለት ለመድረኩ መሪዎች እንደመለስሉዋቸው ሊታወቅ ተችለዋል፣
     በማስከተል በስብሰባው መድረክ የተገኘው ህብረተሰብ። ቅድምያ ለህዝቡ ስለ ወንጀል መከላከል ከማስተማራውቹህ በፊት በናንተ ላይ እየተፈፀመ ያለው ወንጀል፤ የመልካም ኣስተዳደር ጉድለትና በዘመድ ኣዝማድና ጥቅም ተሳስራቹህ የምትፈፅሙት ፍትሃዊነት የሌለው ኣሰራራቹህ ማጥራትና ማስተካከል ኣለባቹህ በማለት ብሶቱ እንደገለፁ ከቦታው የደረሰን መረጃ ጨምሮ ኣስረድተዋል፣
     በመጨረሻም የከተማው ህዝብ ዋነኛዎቹ የመንግስት ፅ/ቤቶች ይከተሉት ካለ መጥፎ እሰራር ወጥተው በቅንነት ህዝቡን ማገልገል የሚችሉበት መንገድ ሳይከተሉ። ስለ ወንጀል መከላከል ኣስመልክቶ ሊሰጠን ታስቦ ያለው ትምህርት። የሚሰጠን ጥቅምና የሚያመጣልን መሰረታዊ ለውጥ የለም፣ መጀመርያውኑ ለህዝቡ ማፈናፈኛ ኣሳጥቶት የሚገኘው የመብትና የፍትህ ጉዳይ ማስተካከል ይገባቹሃል በማለት ስብሰባውን ረግጦ እንደተበተነ መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣