Tuesday, January 7, 2014

በባህርዳር ከተማ ውስጥ ለኮንደምንየም ቤት መስርያ ተብሎ የተዘጋጀ መሬት የፕሮጀክቱ ስራ ኣስከያጆች እናዳሻቸው እየሸጡ ለራሳቸው ጥቅም እያዋሉት መሆናቸው የደረሰን መረጃ ኣስታወቀ፣




መረጃው ኣንደገለጸው በኣማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ውስጥ በቀበሌ 16 ኣካባቢ ለኮንደሚንዮም ቤት መስርያ ተብሎ ተመርጦና ተከልሎ ለተዘጋጀ ቦታ ኣቶ መግስቱ ገብረመድህን የተባለው የፕሮጀክቱ ሃላፊ ለባለ ሃብቶች እየሸጠ የግሉን ሃብት እያከማቸበት ኣንዳለ ተገለፀ፣

     ኣቶ መንግስቱ ገብረመድህን የተሰጠው ህዝባዊ ሃላፊነት ወደ ጎን ትቶ የግል ጥቅሙ በማስቀደም በታህሳስ 20/2006 ኣ/ም ሰዎስት መቶ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መሬት ለኣንድ በለ ሃብት በኣንድ መቶ ኣርባ ሺ ብር እንደሸጠለትና ለዚሁ ህገ ወጥና ብልግና የተሞላበት ኣሰራር ኣስመልክቶም ያካባቢው ነዋሪ ህዝብ ተቃውሞው እያሰማ እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል፣

     ከተቃዋሚዎቹ ኣንዳንድ ለመግለፅ

- ኣቶ ደምሴ ፋንታሁን
- ኣቶ ኣረጋው
- ቄስ ኢሳያስ ኣያሌውና ሌሎችም እንደሚገኙበት መረጃው ኣክሎ ኣስረድተዋል፣