በኢትዮ-ጅቡቲ መስመር ላይ በተለያዩ ተሽከርካሪዎችና
የጭነት እንስሳዎች እየተጠቀሙ ከቦታ ወደ ቦታ የሚነግዱ ዜጎች ራሳቸው ስራ ፈጥረው ባገኙት ገቢ የቤተስዎቻቸዉ ኑሮ በመለወጥ የተሻለ
ዉጤት እንዳገኙ መረጃው ቢጠቁምም፤ በኣከባቢው የሚገኙ የስርኣቱ ወታደሮች
እና ታጣቂ ምልሻዎች ግን የማይገባቸው ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ከግምሩክ ተቆራኝተው ባቃራጭ ወደ መንግስት እጅ ሳይገባ ንብረታቸው እየወሰዱት
መሆኑን ያገኘነው መረጃ ኣስታወቀ፣
በኣካባቢው ከነጋዴዎቹ የሚነጠቁ የህዝብ ንብረት በሃላፍነት እንዲቆጣጠር በጅጅጋ
ከተማ የግሙሩክ ዋና ሃላፊ ሁኖ የተመደበ ኮለኔል ሃይለ ተክሌ፤ ታሕሳስ 12 2006 ዓ/ም በግምጃ ቤቱ ሲሰበሰብ የቆየ ዉድ የሆነ
ንብረት ለይቶ በሁለት ተሽከርካሪዎች በመጫን እንደተሰወረና የገባበትን ኣድራሻ ባለ መታወቁ ንብረታቸው የተወሰዳቸው ዜጎች እንዲመልስላቸው
በህግ ፊት ቀርበው ቢከራከሩም፤ እስካሁን መፍትሄ ሊያገኙ እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችለዋል፣