Saturday, January 4, 2014

በሸራሮ ከተማ የንግድ ፍቃድ ሳይኖራቸው የጠጠር ድንጋይ ጭነው ወደ ቤታቸው እየወሰዱ ለነበሩ ሰዎች ባት ባልከፈለች መኪና ጫናቹህ ተብለው እየተንገላቱና እየተቀጡ መሆናቸው ታወቀ፣




በመረጃው መሰረት ኣቶ ገብረሃወርያ እምባየ የተባለ የሸራሮ ከተማ ነዋሪ በታሕሳስ 19 2006 ዓ/ም የግል ስራው ለማፋጠን ብሎ በራሱ የጭነት ተሽከርካሪ የጠጠር ድንጋይ ጭኖ ወደ ቤቱ በመጣበት ግዜ፤ ያለ ምንም ማስጠንቀቅያ የከተማዋ ኣስተዳዳሪዎች ለዚሁ ስራ የሚመለከት ያወጣሀው የንግድ ፋቃድ የለህም በማለት መኪናዋን  ለሁለት ቀን ኣቁመው 5000 ብር ቀጥተው እንደለቀቁዋት ኣስገነዘበ፣
ምክንያት እየፈጠርክ የህዝብ ገንዘብ መዝመት እንደ እለታዊ ስራቸው ወስደው በመንቀሳቀስ የሚገኙ የሸራሮ ከተማ ኣስተዳዳሪዎች ኣቶ እምባየ ሆኑ ሌሎች ባለ ሃብቶች፤ ከባለስልጣኖቹ ጋር በመቆራኘት ጉቦ ባለ መስጠታቸው ሃላፍነታቸው ተጠቅመው ህጋዉነት የሌለው ቅጣት እየወሰኑ ከስራቸው እንዲስተጓጎሉ እያደረጉ እንደሚገኙ ያገኘነው መረጃ ኣስታዉቀዋል።