በመረጃው መሰረት ይህ በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ታህታይ ቆራሮ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ ከእያንዳዱ ቀበሌዎች
አስር አስር ሰዎች የተወከሉበት ስብሰባ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ስታዲዮም ለአንድ ሳምንት ያህል እንደተካሄደና የስብሰባው
አጀንዳም ማንኛውም መሬት ያለውና የሌለው ገበሬ ማዳበርያ መውሰድ እንዳለበት፤ ፀጉረ ለወጥ ለሆኑ ሰዎች ተከታትለህ በመያዝ መረጃ
መስጠትና። ቀጣይ ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ላይ እያንዳንዱ አባል ለሚሰጠው የስራ ድርሻ በቂ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ በሚል ትኩረት
ሰጥተው ለማሳመን ቢመኩሩም። ተሰብሳቢዎቹ ግን ማንኛውም ድጋፍ ወይም ተቃውሞ ሳያቀርቡ በዝምታ እንዳለፉት ለማወቅ ተችለዋል፣
ይህ የመለስ የተሃድሶ ዘመቻ ለሰላም፤ ለልማትና ለዴሞክራሲ የሚል ቃል አንግበው
ያካሄዱት ስብሰባ። አላማው አብዛኛው የታችኛው የህበረተሰቡ ወገን ለሆነው አካል። የህወሃት አባል ለማድረግና የስርዓቱ እድሜ ለማራዘም
ተብሎ የተካሄደ እንደሆነ የገለፀው መረጃው፤ የታህታይ ቆራሮ ወረዳ ህዝብ ግን እንደሌላው የትግራይ ህዝብ የስራዓቱ ተንኮል አበጥሮ
በማወቁ ምክንያት። ለአንድ ሳምንት ያህል ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶበት በተካሄደው ስብሰባ ላይ ህዝቡ ምንም ሃሳብ ሳይሰጥበት እንደተገባደደ።
ከስብሰባው ውስጥ ከተካፈሉት ምንጮጫችን የደረሰን መረጃ አስታውቋዋል፣