Sunday, February 2, 2014

በትግራይ ምእራባዊ ዞን የተመደቡ የመንግስት ሰራተኞች ህዝቡን ለማገልገል ሳይሆኑ የሃገርና የህዝብ ሃብት ለመመዝበርና ንሮኣቸውን ለማሳደግ እንደሆነ የሁመራና የኣካባቢው ነዋሪ ህዝብ ገለፀ፣




በትግራይ ምእራባዊ ዞን ውስጥ በሚገኙ የዞንና የወረዳ ጽሕፈት ቤቶች ውስጥ የሚመደቡ ሃላፊዎችና ተራ ሰራተኞች። የተሰጣቸውን የስራ ዘርፍ ወደ ጎን ትተው ህጋዊ ባልሆኑ ተግባሮች በመሰማራት። ከልክ ያለፈ ሃብት በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኙና። ይህም ተግባር የተለመደ አሰራር እንደሆነ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል፣
     በተለይ በህወሃት አመራር ፖለቲካዊ ስልጣን ተሰጥቶዋቸው ወደ ዞኑ እየተመደቡ ያሉ ካድሬዎች። የተሰጣቸውን ስልጣን ተጠቅመው ከልክ ያለፈ ጉቦ በመቀበል የአገርና የህዝብን ሃብት በመመዝበር። በተወሰነ ዓመት ውስጥ ባለ ሃብት ለመሆን ሲበቁ። ጭቁኑ ህዝብ ግን በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት የድህነት ኑሮ እንዲመራ ግድ እንደሆነበትና። ባገኘው አጋጣሚም እየታየ ላለው አስነዋሪ ተግባር አስመልክቶ ደጋግሞ በመግለፅ ላይ እንደሆነ። ከአካባቢው የተገኘው መረጃ ገልፀዋል፣
     የሁመራና የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ ከመንግስት ሊያገኘው የሚገባውን ህጋዊ የሆነ አገልግሎት ባለማግኘቱ ምክንያት። ስራውን ለማስፈፀም ሲል ወደ እያንዳንዱ ጽሕፈት ቤት በሚሄድበት ግዜ በየደረጃው ላሉ አስፈፃሚዎች ጉቦ እንዲከፍል ተገደዋል ያለው መረጃው። በአሁኑ ግዜ ግን በዚህ ዓይነት መንገድ መጓዝ ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት አይቻልም ከሚል ሃሳብ ተነስቶ ባገኘው አጋጣሚና የስብሰባ መድረክ ብሶቱን እያሰማ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችለዋል፣


   በመጨረሻ! ይህን የህዝቡን ብሶት መሰረት ያደረገ መረጃ። በዞኑ ውስጥ ተገቢነት በሌለው መንገድ ይህዝቡን ሃብት መዝብረው በተወሰነ ግዜ ባለ ሃብት ከሆኑት የመንግስት ሰራተኛ ውስጥ መምህር ፍርደድንግል የተባለ የሚገኝባቸው ሌሎችም እንዳሉ መረጃው አክሎ አስረድተዋል፣