በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ውስጥ በሚገኝ እስር ቤት
ያሉ እስረኞች። ለስርዓቱ አስጊ ናቸው በሚል ምክንያት ለረጅም ግዜ ተጨባጭነት በሌለው መንገድ በአሰቃቂ ሁኔታ ታስረው የነበሩ ወገኖች።
በጥር 15 2006 ዓ/ም ለሽንት ከወጡ በኃላ ለመሸሽ ሞኩረዋል በሚል ቅጥፈት የተሞላው ምክንያት። እስረኞቹን እየጠበቁ በነበሩ
ፖሊሶች በተተኮሰው ጥይት። በርካታ ሙትና ቁስለኛ እንደሆኑ የዓይን እማኞችን መሰረት ያደረገ መራጃ ኣስታወቀ፣
እነዚህ የተገደሉትና የቆሰሉት ወገኖች በመንግስት ላይ ጉዳት ለማድረስ አስባችሁ
ነበር ተብሎ ለቀረበላቸው መሰረት ለሌለው ውንጀላና። እንዲያምኑ ተብለው በላያቸው ላይ በፖሊሶቹ የተፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት ምርመራ
ለውጥ ማምጣት ስላልቻለ። በመጨረሻ የተለያዩ ተንኮሎች በመፍጠር እንዲገደሉና እርምጃ እንዲወሰድባቸው እንደተደረገ መረጃው ጨምሮ
አስረድተዋል፣
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሽሬ ከተማና የአካባቢው ነዋሪ ህዝብ። ስርዓቱ ባካሄደው
አረሜናዊ ተግባራት። በየደረጃው በተቀመጡት የዞኑ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ላይ የነበረው የጥላቻ መንፈስ ይበልጥ እንደጨመረለትና።
ለስርዓቱ ያለው እምነት እየወረደ ነው ያለው መረጃው። በተከሰተው ዘግናኝ ሁኔታም በህዝቡ ውስጥ ነጋጋሪ አጀንዳ ሆኖ እንዳለ ከቦታው
ለማወቅ ተችለዋል፣