Sunday, February 2, 2014

በአማራ ክልል የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ አልሰራችሁም በሚል ምክንያት ህብረተሰቡን የማሰርና መቅጣት ተግባር ተባብሶ እየቀጠለ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገለፁ፣




   በአማራ ክልል አዊ ዞን ባንጃ ወረዳ ወትላ-ክንድካን፤ ክንድካንና ቆማውስን ቀበሌዎች የሚኖሩ አንዳንድ ወገኖች በእድሜ የገፉ፤ጤና ያጡና የመሳሰሉ ችግሮች እንዳሉባቸው እየታወቀ። በአካባቢው ባሉ አስተዳዳሪዎች የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ አልሰሩም በማለት። ፀረ ልማትና የልማት እንቅፋቶች ናቸው የሚል ስም እየሰጡ አስርው በገንዘብ እየቀጥዋቸው እንዳሉ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
   የዚህ ችግር ሰላባ የሆኑ ሰዎች በበኩላቸው ችግራችንን የአካባቢው ህብረተሰብ እያወቀው ለምን እንታሰራለን እንቀጣለን የሚል ጥያቄ አስነስተው ወደ ሚመለከታቸው አካልት ያቀረቡ ቢሆኑም። እስካሁን ለጉዳዩ ትኩረት የሰጠ ባለስልጣን እንደሌለና። ይህ የስርዓቱ ብልሹ የሆነ አካሄድም በከፋ መልኩ እየቀጠለ መሆኑንና። ከዚህ የተነሳም ህዝቡ በስርዓቱ ላይ ያለው እምነት ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ ስለመጣ። አንድ ቀን የህዝቡ ስሜት ፈንድቶ በስርዓቱ ላይ ከባድ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል መረጃው አክሎ አስረድትዋል፣