በመረጃው መሰረት በትግራይ ሰሜናዊ
ምዕራብ ዞን የሚገኝ የደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም ጽሕፈት ቤት በዚህ ሰሞን ከ70 በላይ ሰራተኛ ለመቅጠር እንደሚፈልግ ባወጣው
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ መሰረት 2,107 ዜጎች ለውድድር የቀረቡ ሲሆኑ፤ ከነዚህ ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተፈትነው ያለፉት 55
ሰዎች ብቻ እንደሆኑ የገለፀው መረጃው፤ የተቋሙ ሓላፊዎች ግን አስቀድመው ጉቦ ለሰጡና ለቤተሶቻቸው ለሆኑ 15 ሰዎች ከ55ቱ ዜጎች
ጋር በህጋዊ መንገድ ተወዳድረው እንዳለፉ አስመስለው በተቋሙ ውስጥ የስራ እድል እንደፈጠሩላቸው ውስጥ አዋቂዎች ከጽሕፈት ቤቱ ባደረሱን
መረጃ ለማወቅ ትችልዋል፣
በትግራይ ክልል ስራ ዓጥነት ከማንም
ግዜ በላይ ተባብሶ እንዳለ የገለፀው መርጃው። በዚህች አንድ የስራ ማስታወቂያ ይህን ያክል ስራ ፈላጊ የሰው ሓይል መመዝገቡ በቂ
ማስረጃ ነው ካለ በኋላ። ሁሉም ለመቀጠር ተመዝግበው ከነበሩ
2,107 ሰዎች አብዛኛዎቹ በማስትሬት ድግሪና ከዚያ በታች የተመረቁ ቢሆኑም። የስራዉን እድል ያገኙት ግን አስቀድመው ጉቦ የሰጡና
ቤተሰቦቻቸው። የተመረቁበት የትምህርት ደረጃም ከዲፕሎማ ያለፈ እንዳልሆነ መረጃው አክሎ አስረድትዋል፣